Sunday, September 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹አርቲስት አስናቀች ወርቁ የኢትዮጵያ ባህል ተምሳሌት ናት››

‹‹አርቲስት አስናቀች ወርቁ የኢትዮጵያ ባህል ተምሳሌት ናት››

ቀን:

የፊልም ዳይሬክተር ራሔል ሳሙኤል

ክራር ሲነሳ በብዙዎች ሕሊና ቀድማ የምትመጣው አስናቀች ወርቁ ናት፡፡ ሙዚቃዎቿ ዛሬም እንደ አዲስ ይደመጣሉ፤ እንደተወደዱም ዘልቀዋል፡፡ የዝነኛዋን ድምፃዊት የሕይወት ታሪክ የሚያሳይ ፊልም በቅርቡ ተሠርቷል፡፡ ‹‹አስኒ፤ ዘ ላይፍ ኦፍ አስናቀች ወርቁ ከሬጅ፣ ፓሽን ኤንድ ግላመር ኢን ኢትዮጵያ›› (የአስናቀች ወርቁ ሕይወት፤ ጥንካሬ፣ ፍቅርና ግርማ ሞገስ በኢትዮጵያ) የተሰኘው ፊልም ዳይሬክተር ራሔል ሳሙኤል ናት፡፡ ከወራት በፊት ለዕይታ የበቃው ፊልሙ በ12ኛው ሼባ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከሚታዩ የኢትዮጵያ ፊልሞች አንዱ ነው፡፡

የዘንድሮው ሼባ ፌስቲቫል ከኢትዮጵያና ከእስራኤል የተውጣጡ ፊልሞች እንደሚስተናገዱበት ቤተ እስራኤል ኦፍ ኖርዝ አሜሪካን ካልቸራል ፋውንዴሽን አስታውቋል፡፡ በዓመታዊው ፌስቲቫል ላይ ከሚቀርቡት ፊልሞች መካከል የእስራኤላውያኑ ፊልም አዘጋጆች ባዚ ጌቴና ሐጋይ አራድ ሥራ የሆነው ‹‹ሬድ ሌቪስ›› ተጠቃሽ ነው፡፡ የእስራኤላውያኑ የፊልም ባለሙያዎች ቤን ሹዳርና ኒኮ ፍሊፒደስ የሠሩት ‹‹ ዘ ቪሌጅ ኦፍ ፒስ››ም በፌስቲቫሉ ይታያል፡፡

‹‹አስኒ›› የሚታየው ሰኔ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. በጽዮን ካፌ ነው፡፡ የፊልሙ አዘጋጅ ራሔል ስለአስናቀች ስትናገር፤ ‹‹የአራት ዓመት ሕፃን ሆኜ በአባቴ ሬዲዮ ፍፁም የምታስገርም ድምፃዊት ሰማሁ፤ የማላውቀው ስሜት ወረረኝ፡፡ አስናቀች በልቤ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የያዘችው ከዛን ወቅት ጀምሮ ነው፤›› በማለት ነው፡፡

ከአሠርታት በኋላ የአስናቀችን ሕይወት የሚያስቃኝ ፊልም ለማዘጋጀት በመቻሏ ዕድለኛ እንደሆነች ትናገራለች፡፡ ‹‹ይህች አስገራሚ አርቲስት አስናቀች ወርቁ የኢትዮጵያ ባህል ተምሳሌት ናት፤›› ስትል ትገልጻታለች፡፡ ራሔል አስናቀች ለኢትዮጵያውያን ያላትን ቦታ አሜሪካውያን ለቢሊ ሆሊደይ ፈረንሳውያኑ ደግሞ ለኤድት ፒያፍ ከሚሰጡት ቦታ ጋር ታነፃፅረዋለች፡፡

‹‹አስናቀች ሕይወቷን ያሳለፈችው በምትወደው ሙያው ውስጥ ጥበባዊነት በተሞላው ሁናቴ ነው፤›› የምትለው የፊልም አዘጋጇ፣ አስናቀችን በ1950ዎቹና 60ዎቹ በኢትዮጵያ ከነበረው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዐውድ ነጥሎ ማየት እንደማይቻል ትገልጻለች፡፡

በወቅቱ የነበረው ወግ አጥባቂ ማኅበረሰብ ለሙዚቀኞች ይሰጥ የነበረውን ዝቅተኛ አመለካከት ታጣቅሳለች፡፡ ድምፃውያን ‹‹አዝማሪዎች›› በሚል ተቀጥላ ስም እየተጠሩ ዝቅ ተደርገው ይታዩ እንደነበር ትናገራለች፡፡ በሃይማኖት ‹‹ገነት የማይገቡ›› በሚል እንደተጠሩ በመግለጽ ‹‹ይህ እውነታ በአገሬ ሙዚቃና ባህል ውስጥ እንዳለ ሁሉ በአስናቀች የሙዚቃ ሕይወት ውስጥም ያለ ነው፤›› ትላለች፡፡ አስናቀች ያለፈው ዘመን ኢትዮጵያና የዛሬው አካልና የዘመናቱ ውጤት መሆኗን ራሔል ታክላለች፡፡

ሼባ ፊልም ፌስቲቫል የሚካሄደው በጄሲሲ ማንሐተንና ጽዮን ካፌ ሲሆን፣ መክፈቻው ግንቦት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. በማንሐተን ይሆናል፡፡ ‹‹ሬድ ሌቪስ›› በመክፈቻው ዕለት ይቀርባል፡፡ ፊልሙ መስጋንዮ ተድላ ስለሚባሉ የ74 ዓመት አዛውንት ይተርካል፡፡ አዛውንቱ ጠንካራ ቢሆኑም መጨነቅ ያበዛሉ፡፡ የ28 ዓመት ወጣት ሳሉ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ይሰደዳሉ፡፡ እስራኤል በሚኖሩበት ጊዜ ባህላቸውን ለመጠበቅ ይጣጣራሉ፡፡

አዛውንቱ ብዙም አይነጋገሩም፤ በተለይ በዕብራይስጥ ‹‹ሒብሩ›› ቋንቋ አይነጋገሩም፡፡ ባለቤታቸው ከሞተች በኋላ የብቸኝነት ኑሮንና ከሰው ተነጥሎ መሞትን አጥብቀው ይፈራሉ፡፡ የኢትዮጵያን ባህል ለመጠበቅ የሚጣጣሩና እሳቸውን የሚመስሉ ሰዎች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መሆኑን ይገነዘባሉ፡፡ ከእውነታው ጋር እየታገሉ የራሳቸውን መንገድ ተከትለው ሕይወታቸውን ለመምራት የሚያደርጉትን ጥረትም ፊልሙ ያሳያል፡፡

‹‹ሬድ ሌቪስ›› የተሠራው እ.ኤ.አ. በ2014 ሲሆን፣ የ80 ደቂቃ ርዝማኔ አለው፡፡ በዕብራይስጥና አማርኛ ሰብ ታይትል የተዘጋጀው ፊልሙ ሼባ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ከሚቀርቡ ፊልሞች የመጀመርያው እንዲሆን ተመርጧል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...