የሥዕል ዐውደ ርዕይ
ዝግጅት፡- ‹‹ኢንተርኔሽን ዓርት›› በተሰኘ የሥዕል ዐውደ ርእይ ከቱኒዚያ፣ ከጅቡቲ፣ ከግብፅ ከፈረንሣይና ሌሎችም አገሮች የተውጣጡ ከ60 በላይ ሥዕሎች ይቀርባሉ፡፡
ቀን፡- ሚያዝያ 28፣ 2007 ዓ.ም.
ሰዓት፡- 12፡30
ቦታ፡- አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ ጋለሪ
አዘጋጅ፡- አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ
*****
የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ
ዝግጅት፡- ከሰሜን አፍሪካና ከመካከለኛው ምሥራቅ የተውጣጡ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ያዘጋጁት የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት
ቀን፡- ሚያዝያ 29
ሰዓት፡- 12፡30
ቦታ፡- ጎተ ኢንስቲትዩት ጋለሪ
አዘጋጅ፡- ጎተ ኢንስቲትዩት
******
የዳንስ ትርዒት
ዝግጅት፡- ‹‹ቢትዊን አስ›› የተሰኘ የኮንቴምፖረሪ ዳንስ ትዕይንት
ቀን፡- ሚያዝያ 29
ሰዓት፡- ከምሽቱ 12፡30
ቦታ፡- አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ
አዘጋጅ፡- አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝ
******
ምርቃት
ዝግጅት፡- ሚውዚክ ሜይ ዴይ በሥዕል፣ በሙዚቃ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በፊልም በባህላዊ ውዝዋዜና በዘመናዊ ዳንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል፤ ተመራቂዎቹም ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
ቀን፡- ግንቦት 1
ሰዓት፡- 3፡00
ቦታ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
አዘጋጅ፡- ሚውዚክ ሜይዴይ
*****
ፊልም
ዝግጅት፡- ‹‹ኢንካውንተርስ፤ እሥራኤሊ ኤንድ ጀርመን ፊልም ደይስ›› በሚል ለአራት ቀናት የሚቆይ የፊልምና ውይይት ዝግጅት
ቀን፡- ግንቦት 3 ‹‹ኤንድ አሎንግ ካም ቱሪስትስ›› ፊልም፣ ግንቦት 4 ‹‹ኢጎር ኤንድ ዘ ክንራንስ ጆርኒ›› ፊልም፣ ግንቦት 5 በፊልም ዙሪያ ውይይትና ግንቦት 6 ‹‹ጎ ፎር ዙከር›› ፊልም ይስተናገዳሉ፡፡
ሰዓት፡- 12፡30
ቦታ፡- ጎተ ኢንስቲትዩት አዳራሽ
አዘጋጅ፡- ጎተ ኢንስቲትዩት