ሰውዬው ጀብደኛነቱን ሲገልጥ ‘‘ጥንቸልዋ ስትሮጥ የኋላና የፊት እግርዋን ጆሮዋን ጭምር በአንድ ጥይት አቦነንኩት፤’’ አለ፡፡ ጓደኛው ግን ‘‘ኧረ እንደሚመስል አድርገህ አውራ! የኋላና የፊት እግርን ከጆሮ ጋር ምን አገናኝቷቸው ነው ይህን ሁሉ የአካል ክፍል በአንዲት ጥይት መምታት የምትችል?’’ አለው፡፡ ተኳሹም ሲመልስ ‘‘በኋላ እግሮችዋ ጆሮዋን ስታክ ነው፤’’ ብሎ ነበር፡፡ ግን ‹‹አንዱ የኋላ እግርስ እሺ ተመታ እንበል፣ የፊት እግሮቿስ ከጆሮ ግንድ ጋር አብረው እንዴት ተመቱ? ስለዚህ ‘‘ነብር ሳይገድሉ ቆዳውን ለመሸጥ ያስማማሉ፤ እንደሚባለው ነው፡፡ ፈጽሞ አንተ አልተኮስህም፣ ጥንቸሏም አልሞተችም’’ አለው፡፡
- መጋቤ አዕላፍ መክብብ አጥናው ‹‹ሁለገብ የአዕምሮ ማዝናኛ›› (2005)