Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየኢትዮ- አውሮፓ ሙዚቃዊ ኅብር በግርማ ይፍራሸዋ

የኢትዮ- አውሮፓ ሙዚቃዊ ኅብር በግርማ ይፍራሸዋ

ቀን:

‹‹ግርማ ይፍራሸዋ ይህን መሰል ሙዚቃ የሚጫወትበት ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥ የለም፡፡ ኢትዮጵያ ያለው ታዳሚ ትኩረቱን ያደረገው በባህላዊ ሙዚቃ እንጂ በክላሲካል ሙዚቃ አይደለም፤›› የሚል አስተያየት ለዘ ዋሽንግተን ፖስት የሰጠው አንድ አሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ነው፡፡

በቅርቡ ግርማ አሜሪካ ውስጥ ያቀረበውን ኮንሰርት የታደመው ኢትዮጵያዊ በአግራሞት ተሞልቶ የተናገረው ነበር፡፡ ፒያኒስትና ሙዚቃ አቀናባሪ ግርማ በኢትዮጵያም ይሁን በአሜሪካ በልዩ ተሰጥኦው ይታወቃል ብሏል፡፡

በቅርቡ በአሜሪካው ቤተስዳ ብሉዝ ኤንድ ጃዝ ሱፐር ክለብ ሙዚቃዎቹን ያስደመጠው ግርማ፣ በአይኤስ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የሚሆን ሙዚቃም ተጫውቷል፡፡ ከወራት በፊት የለቀቀው አልበም ‹‹ፒስ ኤንድ ላቭ›› በዛው አሜሪካ ሪከርድ የያዘ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ‹‹ሰመመን›› የተሰኘው ሙዚቃ የዓመቱ ምርጥ የክላሲካልና ብሉዝ ሙዚቃ ሆኗል፡፡

ዋሽንግተን ፖስት ግርማ ሙዚቃውን ስላቀረበበት የሙዚቃ ኮንሰርት በዝርዝር ዘግቧል፡፡ ‹‹ከዓመቱ ምርጥ የሙዚቃ ኮንሰርቶች አንዱ በሆነው ዝግጅት የአውሮፓውያን ፒያኖ ጨዋታ ተሞክሮውን በኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ አሳይቷል፤›› ብሏል፡፡ የቾፒንና ሹማን ሙዚቃዎች ላይ ልዩ ሪትም ጨምሮበት ማስደመጡ የሙዚቃውን ውበት እንዳጐላው ተገልጿል፡፡ ‹‹ኦተም›› የተሰኘውን የቲቻኮቮስኪ፣ የሊስዝትን ‹‹ኮንሶሌሽን ነምበር 3›› እና የጄምስ ሊ ‹‹ሜሞሪስ ኦፍ አክሱም›› እንዲሁም ራሱ ያቀናበራቸውን ሙዚቃዎች ተጫውቷል፡፡

በዕለቱ ‹‹ላቭ ኤንድ ፒስ›› ከተሰኘው አልበሙ መርጦ ካቀረባቸው ሙዚቃዎቹ መካከል በኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃ ላይ ተመሥርተው በአውሮፓ ቴክኒክ የቀረቡት ይጠቀሳሉ፡፡ ‹‹እልልታ›› እና ‹‹ባለ ዋሽንቱ እረኛ›› ከቀረቡት ሙዚቃዎች መካከል ሲሆኑ፣ ‹‹አምባሰል›› ባህላዊ ሙዚቃን በቤትሆቨን ዘዬ ማቅረቡም ተመልክቷል፡፡

ግርማ ምሽቱን ያደመቁና ተወዳጅ ድባብ የፈጠሩ ሙዚቃዎችን እንዳቀረበ በመዘርዘር ‹‹አውሮፓ ውስጥ ሙዚቃ ያጠናውና አሜሪካ ውስጥ ኮንሰርት ያቀረበው ሙዚቀኛ በርካታ አስገራሚ ሥራዎች አስደምጧል፤›› ተብሏል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...