Thursday, July 25, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ምርት ገበያው የአባልነት መቀመጫን በ1.6 ሚሊዮን ብር ሸጠ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ የአንድ አባልን መቀመጫ ለማስተላለፍ ባወጣው ጨረታ በ1.62 ሚሊዮን ብር ተሸጠ፡፡ ምርት ገበያው ሚያዝያ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ለ16ኛ ጊዜ ባካሄደው ጨረታ ወንበሩን ለመግዛት የተጫረቱት ሁለት ብቻ ነበሩ፡፡

በዚሁ መሠረት ከቀረቡት ሁለት ተወዳዳሪዎች መካከል አቶ ዓባይነህ ዘርፋአለነህ የተባሉ ተወዳዳሪ 1.62 ሚሊዮን ብር ዋጋ በመስጠታቸው አሸናፊ ሊሆኑ መቻላቸውን ከምርት ገበያው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ለዚህ ጨረታ የቀረበው ወንበር በመጀመሪያ ተገዝቶ የነበረው 50 ሺሕ ብር ሲሆን፣ አሁን በጨረታ ሲሸጥ ግን መጀመሪያ ወንበሩ ተገዝቶበት ከነበረው ዋጋ በአምስት እጥፍ ብልጫ ሊሸጥ ችሏል፡፡

ምርት ገበያው ከሁለት ወር በፊት ባካሄደው ተመሳሳይ የአባልነት መቀመጫ ጨረታ አኪኮ የተባለው ኩባንያ በ1.61 ሚሊዮን ብር በማቅረብ አሸንፎ የአባልነት መቀመጫውን መረከቡ አይዘነጋም፡፡

የምርት ገበያው ሁለት ዓይነት የአባልነት መደቦች ያሉት ሲሆን፣ አገናኝ አባልና ተገበያይ አባል በሚል የተከፈለ ነው፡፡ ተገበያይ አባል የሚገበያየው በራሱ ስም ብቻ ሲሆን፣ አገናኝ አባል ደግሞ በራሱ ወይም በደንበኞች ስም መገብየት የሚያስችለው እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሠረት አሸናፊ የሆኑት አቶ ዓባይነህ የተገበያይ አባልነትን ለመሥራት የሚያስችላቸው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በአሁኑ ወቅት 346 ሙሉ አባላትን ከ14 ሺሕ በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን፣ ሥራ ሲጀምር በ100 ሙሉ አባላትና በስድስት ሺሕ ደንበኞች እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዘመናዊ ግብይት የተለያዩ ስድስት ምርቶችን እየገበያየ ያለው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሲሆን፣ ዋናዎቹ ቡና፣ ሰሊጥና በሎቄ ናቸው፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች