Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኢትዮጵያና ኬንያ በኦታዋ ማራቶን ለሪከርድ ይጠበቃሉ

ኢትዮጵያና ኬንያ በኦታዋ ማራቶን ለሪከርድ ይጠበቃሉ

ቀን:

በግንቦት አጋማሽ በካናዳ በሚካሄደው የኦቶዋ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያንና ኬንያውያን አትሌቶች የቦታውን ሪከርድ ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡

እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚካሄደው ውድድር ዘንድሮ በዴጉ ማራቶን ያሸነፈው ኢትዮጵያዊ ግርማይ ብርሃኑ ከሦስት ኬንያውያን በተለይም ከፒተር ኪሩይ ጋር የሚያደርገው ፉክክር የቦታው ክብረወሰን ሊሻሻል እንደሚችል መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡት ነው፡፡

ኦል አፍሪካ እንደዘገበው፣ ፒተር ኪሩይ የግል ሰዓቱ 2፡06.31 ሲሆን የግርማይ ሰዓት በፊናው አምና በዱባይ ያስመዘገበው 2፡0.49 ነው፡፡ ሌላው ተወዳዳሪ ያገሩ ልጅ ዳዲ ያሚ ከሦስት ዓመት በፊት በዱባይ 2፡05.41 ማስመዝገቡ ይታወሳል፡፡ ሦስተኛው ኢትዮጵያዊ ተወዳዳሪ የ2001 ዓ.ም. ቦስተን ማራቶን አሸናፊው ድሪባ መርጋ ነው፡፡

ሌሎቹ ኬንያውያን ተወዳዳሪዎች አልፌርስ ላጋትና ፊሊፕ ካንጎጎ በቅደም ተከተል ባለፉት ሰባት ወራት ያስመዘገቡት 2፡07፡11 እና 2፡08፡16 ነበር፡፡

በሴቶች ምድብ የምትጠበቀው የዴጉ ማራቶን ባለድሏ ኢትዮጵያዊቷ መሰለች መልካሙ ናት፡፡ መሰለች በዴጉ ድል ያስመዘገበችው 2፡27.24 የነበረ ቢሆንም ከሦስት ዓመት በፊት በፍራንክፈርት ማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ ድል ስትመታ ያስመዘገበችው 2፡21.01 እንደነበር ይታወሳል፡፡ መሰለች በ2001 ዓ.ም. በዓለም የ10,000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚና ርቀቱን 29 ደቂቃ 53.80 ሰከንድ በመፈጸም የምንጊዜም ሁለተኛው ፈጣንና ምርጥ ጊዜ ማስመዝገቧ ለኦቶዋው ውድድር ተጠባቂ እንዳደረጋት ዘገባው አመልክቷል፡፡ ከርሷ ጋር ኢትዮጵያን የምትወክለው ሌላዋ ተፎካካሪ የአምና የሁስተንና ሮተርዳም ማራቶን አሸናፊዋ አበበች አፈወርቅ ምርጥ ጊዜዋ ዘንድሮ በዱባይ ያስመዘገበችው 2፡23፡33 ነው፡፡ ሦስተኛዋ ኢትዮጵያዊት ተወዳዳሪ የኦታዋ ማራቶን የሁለት ጊዜ አሸናፊዋ የሺ ኢሳያስ ናት፡፡

ኬንያን የሚወክሉት ርብቃ ቼሲርና ኤጀንስ ኪፕሮፕ ያስመዘገቡት ጊዜ 2፡25፡22 እና 2፡23፡54 ሲሆን፣ በተለይ ኪፕሮፕ በዓምናው የኦታዋ ማራቶን ሦስተኛ ሆና ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...