Wednesday, September 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትኢትዮጵያና ጂቡቲ የገጠር ሞተር ባይክ ውድድሮችን አሸነፉ

  ኢትዮጵያና ጂቡቲ የገጠር ሞተር ባይክ ውድድሮችን አሸነፉ

  ቀን:

  የኢትዮጵያ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን (ኢሞስአ) ለዘንድሮ ሁለተኛው የሆነውን ውድድር ሚያዝያ 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በላንጋኖ ሐይቅ አካባቢ አካሄደ፡፡

  ባለፈው እሑድ የተካሄደው የሞተር ባይክ የገጠር መንገድ ላይ ውድድር ‹‹ሞተር ባይክ ኢንዱራሊ- ላንጋኖ›› የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን፣ ዘጠኝ ኢትዮጵያውያንና ስምንት ጂቡቲያውያን ተወዳዳሪዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡

  ኢሞስአ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የሁለቱ አገሮች 17 ሞተር ብስክሌተኞች በሁለት ምድብ ተከፍለው ባደረጉት ከፍተኛ ፉክክር በምድብ አንድ የጂቡቲ፣ በምድብ ሁለት የኢትዮጵያ ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ሆነዋል፡፡

  በምድብ አንድ በ300 ሲሲ ውድድር መሐመድ ነጂብ ከጂቡቲ አንደኛ ሲወጣ ሰይድ መሐመድ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ በምድብ ሁለት ከ301 ሲሲ- 550 ሲሲ ፉክክር ከኢትዮጵያ የቀረቡት ማርሻል ጊሊስ እና ፍላቪዬ ቦናዬቲ አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ፣ የጂቡቲው ፋቢዬ ጋቤሊ በሦስተኛነት ውድድሩን በመፈጸም ሁሉም የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

  ኢሞስአ የዓመቱን የመጀመሪያ የመኪና እሽቅድድም ባለፈው ኅዳር ድሪግ-ሬስ በሚል መጠሪያ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በቤንዚንና ነጭ ናፍጣ ላይ ጭማሪ ተደረገ

  ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ...

  ‹‹ለሰላምና ለዕርቅ መሸነፍ የለብንም›› ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

  የሰው ልጅ ጠብን በዕርቅ፣ በደልን በይቅርታ፣ ድህነትን በልማት፣ ክህደትን...

  መፍትሔ አልባ ጉዞ የትም አያደርስም!

  ኢትዮጵያ ችግሮቿን የሚቀርፉ አገር በቀል መፍትሔዎች ላይ ማተኮር ይኖርባታል፡፡...

  ጦርነቱና ውስጣዊ ችግሮች

  መስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም. የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው...