የአዲስ አበባ ብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ አራተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁለት ወራት ያካሄደው የብስክሌት ውድድር ሚያዝያ 27 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ በአምስት ክለቦች መካከል ከየካቲት 29 ቀን እስከ ሚያዝያ 27 ቀን ድረስ በሁለቱ ጾታዎች በተከናወኑት ልዩ ልዩ ውድድሮች ተሳታፊ የነበሩት እህል ንግድ፣ ሜታ ቢራ፣ ኤሌክትሪክ፣ ጋራድ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዴሚ ቡድኖች ናቸው፡፡ በታዳጊ እና በአዋቂ ማውንቴን ጋራድ እና ኤሌክትሪክ፣ በሴቶች ማውንቴን የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዴሚ ቡድኖች ሲያሸነፉ፣ በኮርስ ብስክሌት የሜታ ቢራ ቡድን ድል ተቀዳጅቷል፡፡ በሁሉም ምድቦች ላሸነፉና ደረጃ ውስጥ ለገቡ ተወዳዳሪዎች እንደየደረጃቸው ከ3,000 ብር እስከ 1,000 ብር ሽልማት መሰጠቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ በፎቶግራፉ ላይ የሚታየው የኮርስ ብስክሌት ምድብ አሸናፊው ሜታ ቢራ ቡድን ነው፡፡