Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየታላቋ ብሪታንያ ምርጫና የዝነኞቹ ሽንፈት

የታላቋ ብሪታንያ ምርጫና የዝነኞቹ ሽንፈት

ቀን:

ታላቋ ብሪታኒያ 56ኛውን የምክር ቤት ምርጫ ያካሄደችው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ተሳታፊ ፓርቲዎች የምርጫው ውጤት ከጠበቁት በላይ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ታዋቂዎቹን ፓርቲዎች ከጨዋታ ያስወጣና አስገራሚም ነበር፡፡ ውጤቱ የምርጫ ሥርዓቱን ለትችት ያጋለጠም ነበር፡፡

በምርጫው የሌበር ፓርቲና የሊበራል ዴሞክራት ፓርቲ ያልተጠበቀ ሽንፈት የገጠማቸው ሲሆን፣ የወግ አጥባቂው ዴቪድ ካሜሩን ፓርቲ ደግሞ አሸንፏል፡፡ ቢቢሲ እንደ ዘገበው፣ ሽንፈቱን መቋቋም ያልቻሉት የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል፡፡ ይህም በፓርቲዎቹ የበፊት አካሄድ ላይ ብዥታን ፈጥሯል፡፡

የወግ አጥባቂው ፓርቲ ተወካይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን ከሊበራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ጋር በመጣመር እ.ኤ.አ ከ2010 ጀምሮ እንግሊዝን የመሩ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2015 በተደረገው ምርጫ ደግሞ 36.9 በመቶ ድምፅ ወይም 331 መቀመጫዎች በማግኘት ፓርቲያቸው አገሪቱን ለሁለተኛ ጊዜ ለመምራት ተመርጧል፡፡

  ምርጫው ያልተገመተ ውጤት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት አላቸው የሚባሉ የቀድሞው ታዋቂ የምክር ቤቱ አባላት በምርጫው ውጤት አጥተዋል፡፡ የሌበር ሻዶው ካቢኔት ሚኒስትሮች ኤድ ባልስና ዳግላስ አሌክሳንደር፣ የስኮቲሽ ሌበር ፓርቲ መሪ ጂም ሞርፊ፣ የቀድሞው የሊበራል ዲሞክራት ሚኒስትሮች ቬኒስ ካብሊ፣ ዳኒ አሌክሳንደር፣ ሲሞን ሂዩስ እንዲሁም ኤድ ዴቪ ሽንፈት የተከናነቡ ሲሆን፣ በሼፊልድ ሃላምኒክ ክሌይ ደግሞ ተመርጠዋል፡፡

ኮንሰርቫቲቯ የኢምፕሎይመንት ሚኒስትር አሽተር ማክ ቬይ በምክር ቤቱ መቀመጫቸውን ካጡት መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ በአጠቃላይ ዝነኞቹ ፖለቲከኞች ሽንፈት የተከናነቡበት ምርጫ ነበር፡፡

የሊበራል ዴሞክራት ፓርቲን የሚመሩት ኒክ ክሌግ፣ እ.ኤ.አ. ከ1970 ወዲህ ፓርቲያቸው ገጥሞት የማያውቀውን ሸንፈት በማስተናገዱ ከሥልጣናቸው ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ የተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክሌግ ፓርቲ ከ57 መቀመጫዎች 49 አጥቷል፡፡ በኤድ ሚልባንድ የሚመራው ሌበር ፓርቲ 30.4 በመቶ ድምፅና 232 መቀመጫ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ዘ ቴሌግራፍ እንደ ዘገበው ፓርቲው እ.ኤ.አ. ከ1987 ወዲህ ከጠበቀው በላይ ከፍተኛ ኪሳራ የገጠመው በዘንድሮ ምርጫ ነው፡፡

በመሆኑም የሌበር ፓርቲው ሚልባንድ እንዲሁም የዩኬ ኢንዲፔንደንስ ፓርቲ መሪ ኒጌል ፋራጅ ከፓርቲ መሪነታቸው ሥልጣናቸውን ለቀዋል፡፡

የዴቪድ ካሜሮን ወግ አጥባቂ ፓርቲ አብላጫ ማለትም 331 መቀመጫ በማግኘት የብሪታንያን ፖለቲከኞች አስደምሟል፡፡ ዘ ታይምስ ዴቪድ ካሜሮንን ጠቅሶ እንደ ዘገበው ከሆነ፣ ዴቪድ ካሜሮን የታላቋን ብሪታንያ ታላቅነት አስጠብቀው ይመራሉ፡፡ በቅስቀሳው ወቅት የገቡትን ቃልም ይተገብራሉ፡፡

ዴቪድ ካሜሮን በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት እንደተናገሩት፣ ፓርቲያቸው ምርጫውን ካሸነፈ አዳዲስ ሥራዎች ይፈጠራሉ፡፡ የኢንተርፕርነርሺፕ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡ እንዲሁም አዳዲስ የመኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ፡፡ የእንግሊዛውያንን ፍላጎትም ያስጠብቃሉ፡፡ የታክስ ክፍያ መጠን ይቀንሳሉ፡፡

ከሌበር ፓርቲ መሪነታቸው ራሳቸውን ያገለሉት ኢድ ሚል ባንድ በምርጫው ባይሳካላቸውም፣ ታላቋ ብሪታንያ እሳቸው ወደሚመኙት ደረጃ ለማድረስ ሁሌም እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡ ሃሬት ኽርማን የፓርቲው የበላይ ጠባቂ ሆነው ተሰይመዋል፡፡

የሊበራል ዴሞክራት ፓርቲው መሪ ኒክ ክሌግ ከምርጫው ሽንፈት በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ የፓርቲ ሥልጣናቸውን የለቀቁት ሽንፈታቸው ልብ የሚሰብር በመሆኑ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

“በምን ምክንያት እንዲህ ያለ ሽንፈት እንደገጠመን ለማወቅና ለመናገር ጊዜው ገና ነው፡፡ ሆኖም ታላቋ ብሪታኒያ አደገኛ ሁኔታ ላይ ደርሳለች፡፡ ጠንካራ አመራር በሌለበት የታላቋ ብሪታንያ የመኖር ጥያቄ እደጋ ውስጥ ነው፤” ብለዋል፡፡

የዩኬ ኢንዲፔንደንት ፓርቲ መሪ ፋራጅ የምርጫ ሥርዓት ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ተሰናባቹ ፋራጅ ለደጋፊዎቻቸው፣ “እኔ የራሴ ዓለም ሰው ነኝ፤” በማለት ደጋፊዎቻቸው ከሥልጣናቸው እንዲያሰናብቷቸው ጠይቀዋል፡፡ የፋራጅ ውድቀት በቀጣይ የፓርቲው ዕጣ ፈንታ ላይ ጥላ እንደጣለ ዘ ጋርዲያን  ዘግቧል፡፡

የምርጫው ውጤት የስኮትላንድ ናሽናል ፓርቲን ያስፈነደቀ ነበር፡፡ ፓርቲው ከ59 መቀመጫዎች 56 ያገኘ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 50 አዳዲስ መቀመጫዎችን የሌበር ፓርቲን በማሸነፍ ያገኘው ነው፡፡

የስኮትላንድ ናሽናል ፓርቲ እ.ኤ.አ. በ2014 በሪፈረንደም ስኮትላንድን ከእንግሊዝ ለመገንጠል አልሞ የነበረ ቢሆንም አልተሳካለትም፡፡ ወግ አጥባቂው ዴቪድ ካሜሮን የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ሥፍራ ይዘው ለመቀጠል ከቻሉ አንድ እንግሊዝ ብቻ እንድትኖር እንደሚሠሩና ምኞታቸው ይህ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ “አንድ ሕዝብ አንድ ኪንግደም” በማለትም በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...