ቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚሌኒየም አዳራሽ አራተኛው የጤና ኤግዚቢሽን ኮንግረስ ተካሂዶ ነበር፡፡ ሆስፒታሎች፣ የሕክምና መሣሪያ አስመጪዎችና የሚመለከታቸው ሌሎችም ተሳታፊ ነበሩ፡፡ የጤና አገልገሎት አሰጣጥ ላይ በሚያተኩረው ኤግዚቢሽን 52 የሚሆኑ የተለያዩ ጤና ማኅበራት፣ በጤናው ዘርፍ ያሉ አምራች ድርጅቶችና አገልገሎት ሰጪዎች ተሳትፈዋል፡፡ በፕሮግራሙ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማስፋፋት፣ ደረጃውን የጠበቀ የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያ አቅርቦት የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡