Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍርፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

ቀን:

‹‹ተቀጣሪው እስከተስማማ ድረስ የትኛውም ቀጣሪ ድርጅት በፈለገው ደመወዝ የማሠራት መብት አለው፡፡››

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ፣ የአዲሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን የቅጥር ደመወዝ አስመልክተው ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአዲሱ አሠልጣኝ ጋር በመሆን በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ የስፖርት ጋዜጠኞች የቀድሞው ዋና አሠልጣኝ ፖርቱጋላዊው ማሪያኖ ባሬቶ 20 ሺሕ ዶላር (ከ400 ሺሕ ብር በላይ) ደመወዝ ያገኙ እንደነበር፣ አሁን ግን አቶ ዮሐንስ በ75 ሺሕ ብር መቀጠራቸውን በተመለከተ ፍትሐዊነቱን ጠይቀው ነበር፡፡ አቶ ጁነዲን ግን ከወራት በፊት ፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ለምን በዚህን ያህል ደመወዝ ተቀጠሩ ብለው በጋዜጠኞች መጠየቃቸውን አስታውሰው፣ አሁን ጥያቄው በሌላ ገጽታ መቅረቡ ትዝብት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡ ተቀጣሪው እስከተስማማ ድረስ ቀጣሪው በፈለገው ደመወዝ እንደሚያሠራ ገልጸው፣ አቶ ዮሐንስም በሚከፈላቸው ደመወዝ ሙሉ በሙሉ መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በአገር ውስጥ ካሉትም የተሻሉ ናቸው ተብሎ ስለታመነባቸው ፌዴሬሽኑ እንደቀጠራቸው አስረድተዋል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...