Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ዙቤይዳ››

‹‹ዙቤይዳ››

ቀን:

‹‹አገር ማለት ሰው ነው እያሉ በትውልድህ እንቅልፍ ላይ ብርድ ልብስ ይደርባሉ፡፡ አገር ማለት አፈር ነው፡፡ ሰውም ማለት አፈር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ የሞቱት ሰዎቻችን ስጋና አጥንት አፈር ሆኖ ይሄው›› አሉና መሬቱን በጎራዴው ጫፍ ጫር አደረጉት፡፡

‹‹አየህ አሁን አፈር አይደለም የጫርኩት፣ የሰው ስጋ ነው! ሲጫር የሚያመው፣ ሲወጋ የሚያቃስት ሰው ነው አፈሩ!! ይሄንን ነው ቆርሰው የሚወስዱት፡፡ አገር ማለት ሰው ከሆነ፣ ሰው አፈር ነውና አፈርህን ሲነኩ እንቢ ልትል ይገባል! ልጄ፣ ሕንፃ እና መንገድ አይግረምህ፣ የሰው እጅ የሚሠራው የእጅ ጥበብ ሁሉ አይድነቅህ፤ ነገም ልጆችህ ከአንተ በተሻለ ይሠሩታልና! ልጆችህ መቼም ለማያገኙት ስንዝር መሬት ግን ያለህን ሁሉ ክፈል…››

ይህ ኃይለቃል የተገኘው በአሌክስ አብርሃም በተጻፈው ‹‹ዙቤይዳ›› በተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ውስጥ ነው፡፡ 22 ታሪኮችን የያዘው ዙቤይዳ፣ 251 ገጾች ያሉት ሲሆን የመሸጪያ ዋጋው 59 ብር ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አሌክስ አብርሃም ከዚህ በፊት ‹‹ዶ/ር አሸብር እና ሌሎችም›› የተሰኘ እንዲሁም ‹‹እናት ፍቅር ሐገር›› የተባለ የግጥም መድበል ለንባብ ማብቃቱ ይታወሳል፡፡

‹‹አባቶችና ልጆች››

የጋዜጠኛና ደራሲ አብርሃም ረታ ዓለሙን ሰባተኛ ዓመት ሙት ዓመት ምክንያት በማድረግ የታተመው መጽሐፍ ‹‹አባቶችና ልጆች እና ሌሎች ታሪኮች›› ይሰኛል፡፡ መድበሉ አብርሃም በሕይወት ሳለ ተርጉሞ ለሕትመት ያዘጋጃቸውን 15 አጫጭር ልቦለዶችን ይዟል፡፡

ጋዜጠኛና ደራሲ አብርሃም በተለያዩ ጋዜጦችና መጽሔቶች በዐምደኝነት ጽሑፎችን በማቅረብ እንዲሁም ‹‹ቢላዋና ብዕር››፣ ‹‹አልን ተባልን አስባልን››፣ ‹‹አባባ ሰው የለም›› እና ‹‹እችክችክ የቃሊቲ እንጉርጉሮዎች›› በተሰኙ መጻሕፍቱ ይታወቃል፡፡ የሪፖርተር፣ አዲስ አድማስ፣ ጽጌረዳ፣ ቁም ነገርና ሩህ ዐምደኛም እንዲሁ በኤፍኤም አዲስ 97.1 የቅዳሜ ጨዋታ አቅራቢም ነበር፡፡

አብርሃም ለዓመታት በመምህርነት አገልግሏል፡፡ በሙዚቃው ዘርፍም ግጥምና ዜማ በመጻፍ፣ በድምፃዊነት፣ በመሣሪያ ተጫዋችነት ይታወቃል፡፡ ሒሩት በቀለ፣ ተሾመ ወልዴና በዛወርቅ አስፋው ግጥምና ዜማ ከሰጣቸው ድምፃውያን ጥቂቱ ናቸው፡፡

‹‹አባቶችና ልጆች›› በ1971 ዓ.ም. በቀይ ሽብር ሰለባ ለሆኑ ጓደኞቹ መታሰቢያነት አዘጋጅቶት የነበረ መጽሐፍ ነው፡፡ 160 ገጽ ያለው መጽሐፍ፣ በ49.55 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ አብርሃም ከዚህ ዓለም የተለየው ግንቦት 11 ቀን 2000 ዓ.ም. ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...