Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናፍርደኞችና ክሳቸው የተቋረጠ እስረኞች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው እንዲፈቱ ተወሰነ

ፍርደኞችና ክሳቸው የተቋረጠ እስረኞች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው እንዲፈቱ ተወሰነ

ቀን:

በተከሰሱበት ወንጀል የተፈረደባቸውና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ በመንግሥት የተወሰነላቸው 746 እስረኞች የሚፈቱት፣ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቦ ከፀና በኋላ የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ነው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሐሙስ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 417 ፍርደኞች ይቅርታ እንዲደረግላቸው በፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ተወስኖ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቧል፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረትም ጉዳያቸው በመታየት ላይ የነበረ የ329 ተጠርጣሪዎችን ክስ ይቋረጣል፡፡

የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መግለጫ እንደሚያስረዳው ይቅርታውና ክስ የማቋረጡ ውሳኔ የተላለፈው፣ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በወሰነው መሠረት ለታሳሪዎች ይቅርታ እንደሚደረግና ክስ እንዲያቋረጥ በመደረጉ ነው፡፡

- Advertisement -

ቦርዱ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ውሳኔ ያሳለፈው ለ124 የኦነግ አባላትና ለ61 የግንቦት ሰባት አባላት ጭምር ነው፡፡ በሃይማኖት አክራሪነት፣ በሁከትና ብጥብጥ ተከሰው ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የተፈረደባቸው መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይቅርታ እንዲደረግላቸው በቀረበው ጥያቄ መሠረት ቦርዱ ውሳኔ ሰጥቷል ከተባሉት ውስጥ በ2004 ዓ.ም. ክስ ተመሥርቶባቸው በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት የተፈረደበት የቀድሞ አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) አመራር አቶ አንዱዓለም አራጌና 18 ዓመታት ጽኑ እስራት የተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚገኙበት አስታውቋል፡፡

ከእነ አቶ አንዱዓለም ጋር በሌሉበት ክስ የተመሠረተባቸው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽና የጋዜጣው ማኔጂንግ ኤዲተር  ጋዜጠኛ ዓቢይ ተክለ ማርያምን ጨምሮ 24 ነበሩ፡፡ ከሁለቱ በስተቀር የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው ናትናኤል መኮንን፣ የመኢዴፓ አመራር የነበረው ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) እና ሌሎችም ከአሥር ዓመታት በላይ ጽኑ እስራት የተፈረደባቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ መዝገብ በሌሉበት ክስ በቀረበባቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ (አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኙ)፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ አቶ መስፍን አማን፣ አቶ ፋሲል የኔ ዓለም፣ አቶ አበበ በለውና አቶ አበበ ገላውን ጨምሮ ሌሎችም ተካተው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ባስታወቀው መሠረት ይቅርታ ከሚደረግላቸው ፍርደኞች ውስጥ 298 በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች የነበሩ ሲሆን፣ 119 ደግሞ በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት የሚገኙ ናቸው፡፡ ክሳቸው ይቋረጣል ከተባሉትም 278 በፌዴራል ማረሚያ ቤት የሚገኙ ሲሆን፣ 33 በትግራይ ክልል ማረሚያ ቤት፣  18 ደግሞ በአማራ ክልል ማረሚያ ቤት የሚገኙ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይቅርታ እንዲደረግላቸው በቦርዱ የተወሰነላቸው 417 ፍርደኞች የሚፈቱት ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቦ ሲፀና የተሃድሶ ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተደረገላቸውም የሚለቀቁት የተሃድሶ ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡

መንግሥት እስረኞችን በሁለት ወራት ውስጥ እንደሚፈታ ካስታወቀበት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በአማራ ክልል 3,503 ተጠርጣሪዎችና ፍርደኞች፣ በኦሮሚያ 2,345 ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች፣ በደቡብ ክልል 413 ተጠርጣሪዎች፣ በትግራይ ክልል 33 ተጠርጣሪዎችና ታራሚዎች፣ እንዲሁም በፌዴራል ደረጃ 413 ተጠርጣሪዎችና ፍርደኞች ክሳቸው እንዲቋረጥና ይቅርታ እንዲደረግላቸው ተወስኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...