Friday, July 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሦስተኛው ዙር የቦክስ ውድድር በጎንደር ተከናወነ

ሦስተኛው ዙር የቦክስ ውድድር በጎንደር ተከናወነ

ቀን:

የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን በዓመቱ ውስጥ ሊያካሂድ ካሰባቸው አራት ዙር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ሦስቱን አካሄደ፡፡ በዚህ መሠረት የመጀመርያ ዙር በኦሮሚያ ክልል ሻሻመኔ ከተማ ሁለተኛው ዙር ደግሞ በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ያካሄደ ሲሆን፣ የሦስተኛው ዙር ውድድር በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ከሚያዝያ 28 እሰከ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ፌዴሬሽኑ የያዘው መርሐ ግብር መሠረት በክለቦች መካከል ውድድር በማድረግ የግልና የቡድን ውጤትን ለመገምገም ማቀዱን ይጠቁማል፡፡ በየክልሉ በመዘዋወር በሚካሄደው ውድድር ስፖርቱ በኅብረተሰቡ ዘንድ ተወዳጅና ተዘውታሪ ለማድረግና ወጣቱን ስለ ስፖርቱ መቀስቀስ ቀዳሚ ዓላማው አድርጎ ተነስቷል፡፡ ከሚያዝያ 28 እና 29 ቀን 2007 ዓ.ም. በየቀኑ 16 ውድድሮች የተካሄዱ ሲሆን፣ በመዝጊያው ዕለት የወርቅና የብር ተወዳዳሪዎች በሁለቱም ፆታ ውድድር አድርገዋል፡፡

በውድድሩ ዘጠኝ ክለቦች ተሳታፊ ሲሆኑ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ ኒያላ፣ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ ኢትዮጵያ ሶማሌ፣ ሐረር ውኃ ፍሳሽ፣ ሐድያና ጎንደር ከነማ ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ ከ49 ኪሎ ግራም እስከ 81 ኪሎ ግራም መጠን በተደረገው በዚህ ውድድር በሴቶችና በወንዶች ዘርፍ የክልልና የአዲስ አበባ ክለቦች ተመጣጣኝ ፉክክር ማሳየት መቻላቸው፣ ጥሩ ማጥቃትና የመከላከልም የቴክኒክ ብቃት መታየት መቻሉ እንደጠንካራ ጎን መታየታቸውን  ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ በውድድር መሳተፍ የጀመረው የኢትዮጵያ የወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ተወዳዳሪዎች በሁለቱም ፆታ ያሳዩት ብቃትና ችሎታ እጅግ አበረታች ከመሆኑም በላይ፣ ከአካዳሚ  በ43 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪ የሆነው ወጣት እንዳሻው አላዩ እና የ52 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪ ወጣት ገዛኽኝ ፈቃዱ የአካዴሚው ተወዳዳሪዎች ከክለብ ተወዳዳሪዎችና ነባርና አገርን በመወከል ተሳታፊ ተጨዋቾች ጋር በመጫወት ያስመዘገቡት ውጤት በቦክስ ስፖርት አስተማማኝ የሆኑ ተወዳዳሪዎችን ማፍራት እንደሚቻል ፍንጭ ያሳየ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሁለት ቀን የውድድር ቆይታም ፌዴራል ማረሚያ ቤት በ14 ነጥብ አንደኛ፣ አዲስ አበባ ፖሊሰ በ13 ነጥብ ሁለተኛና እንዲሁም በተመሳሳይ ነጥብ በማምጣት ፌዴራል ፖሊስና ኒያላ በ10 ነጥብ ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በኮንጎ ብራዛቪል ለሚደረገው የመላው አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ከቀረቡት ስምንት የውድድር መደቦች በስድስቱ ለመሳተፍ ከተሳታፊዎች ውስጥ 16 ተወዳዳሪዎችን መምረጡን አቶ ስንታየሁ ተስፋዬ የውድድርና የሥልጠና ባለሙያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የ4ኛ ዙር ውድድር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድና ተጨማሪ ተወዳዳሪዎች ከውድድሩ በመምረጥ በቂ የሆኑትን የመለየት ሥራ እንደሚሠሩም ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በጎንደር ለተደረገው የውድድር መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ ድርጅቶችና ክለቦች እንዲሁም ለተወዳዳሪ ስፖርተኞችና ክለቦች የምስክር ወረቀት፣ ሜዳሊያና ዋንጫ ሽልማት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ በመስጠት የተጠናቀቀ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...