Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው የት እንደሚገኙ አላውቅም አለ

መኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው የት እንደሚገኙ አላውቅም አለ

ቀን:

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ወደ ቢሮ አለመምጣታቸውን አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አላውቅም ብሏል፡፡ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረ ገጾች ዘገባዎች ደግሞ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ወደ ኤርትራ ማምራታቸው እየተነገረ ነው፡፡ በትክክል የት እንደሄዱ ግን አልተረጋገጠም፡፡

ካለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በፌስቡክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ተስፋሁን አለምነህ የትጥቅ ትግል ለማድረግ ወደ ኤርትራ ሄደዋል የሚሉ ዘገባዎች የወጡ ቢሆንም፣ የመኢአድ ፕሬዚዳንት አቶ አበባው መሐሪ ግን፣ ‹‹የት እንደሄደ አላውቅም፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ ግን እንደ ማንኛውም ሰው በማኅበራዊ ድረ ገጽ አይቻለሁ፤›› በማለት ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ተስፋሁን ለመጨረሻ ጊዜ መኢአድ ቢሮ የታዩት ድርጅቱ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ለመካፈል ከሁለት ሳምንት በፊት ቅዳሜ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አበባው፣ በመሀል የተፈጠረውን ነገርና ወዴት እንደሄዱ እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡

የፊታችን እሑድ በሚካሄደው አምስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ መኢአድን ወክለው እንደማይወዳደሩ የገለጹት አቶ አበባው፣ አቶ ተስፋሁን ፓርቲውን የተቀላቀሉት ከአሥር ዓመታት በፊት እንደነበረ አክለው ገልጸዋል፡፡

‹‹ፓርቲውን የተቀላቀለው ከጐጃም ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ብሎ ደግሞ የምዕራብ ጐጃም የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ነበር፤›› ብለዋል፡፡

አቶ አበባው ‹‹የድርጅታዊ ጉዳይ አይደለም፡፡ የመኢአድ አባልነት መሥፈርት በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በዚህም መሠረት በፈቃደኝነት አባል ይሆናል፡፡ ለመውጣት ሲፈልግ ደግሞ ይለቃል እንጂ በግድ የሚያዝ ነገር የለም፤›› በማለት ውሳኔው ግለሰቡን ብቻ የሚመለከት እንደሆነና ከፓርቲው ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው አስረድተዋል፡፡

አቶ ተስፋሁን በፓርቲ እንቅስቃሴ ውስጥ ጥሩ ተሳትፎ እንደነበራቸው ያስታወሱት አቶ አበባው፣ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መመረቃቸውንም አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጁ ድርጅቶች ኤርትራ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ፣ ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል ግንቦት 7፣ ኦነግ እና ኦብነግ ነፍጥ አንግበው መንግሥትን ለመጣል አቅደው እንደሚሠሩ ይነገራል፡፡

በቅርቡ መንግሥት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ብርሃኑ ተክለ ያሬድ፣ ፍቅረ ማርያም አስማማውና እየሩሳሌም አስፋው ወደ ኤርትራ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸውና ክስ እንደመሠረተባቸው መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡  

አቶ ተስፋሁን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ የፕሮፋይል ፎቶአቸውን በመለወጥ ታጣፊ ክላሽኒኮቭ አንግተው የሚታዩ ሲሆን፣ ከሰላማዊው ትግል በመውጣት ለትጥቅ ትግል መዘጋጀታቸውን ማሳያ ነው እየተባለ ነው፡፡ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ከዚህ ቀደም የተለያዩ የፉከራና የሽለላ ግጥሞችን በማስፈር የሚታወቁት አቶ ተስፋሁን፣ ኤርትራ ወይም ሌላ ሥፍራ ለትጥቅ ትግል መሄዳቸውን ያረጋገጠ አካል የለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...