Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልየሙዚቀኛው አሻራ

  የሙዚቀኛው አሻራ

  ቀን:

  በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር የተዘጋጀው ሦስተኛው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቀን የተከበረው ከአንድ ወር በፊት ነበር፡፡ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ባለሙያዎች ተሸልመዋል፡፡ ሙዚቀኞቹ ከ1950ዎቹ ጀምሮ በዘርፉ የሚጠቀሱና ሁነኛ ሚና የተጫወቱም ናቸው፡፡ ሽልማቱን ለሙዚቀኞቹ እንዲያበረክቱ ከተጋበዙት አንዱ የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ ሲሆኑ፣ እሳቸውም ልዩ ተሸላሚ ነበሩ፡፡

  ‹‹ሙዚቃ የጀመሩት የ11 ዓመት ልጅ ሳሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ውስጥ ነበር፡፡ በሮሃና በዳህላክ ባንድ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ነበራቸው፡፡ በርካታ ሙዚቀኞችንም ለእውቅና አብቅተዋል፡፡ በአገር ፍቅር ቴአትር ዘመናዊ ሙዚቃ አሠልጥነዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ማኅበር ውስጥ ለዓመታት ለሙዚቀኛው መብት ታግለዋል፡፡ ከኮሜርስ በአካውንቲንግ ተመርቀው በሒሳብ ሹምነት አገልግለዋል፡፡ ሙዚቃ አቀናባሪው የያሬድ ትምህርት ቤት ምሩቅ ሲሆኑ፣ ቫዬሊን፣ ጊታርና ፒያኖም ይጫወታሉ፤›› በሚል ተገልጸው ሙዚቀኛው ሸልማቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡

  በቅርቡ ደግሞ የኚህን ሙዚቀኛ ሕይወት የሚዳስስ ዘጋቢ ፊልም ‹‹የሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ የሕይወት ዘመን ትረካ›› በሚል ርዕስ ተሠርቷል፡፡  ዘጋቢ ፊልሙ ዋነኛ ትኩረቱን ያደረገው በሙዚቃ ሥራዎቻቸው ላይ ሲሆን፣ ከአንድ ሳምንት በኋላ በይፋ ይመረቃል፡፡ ፊልሙ የሙዚቀኛውን ሕይወት ከቤተሰቦቻቸው፣ ከጓደኞቻቸውና ከአድናቂዎቻቸው አስተያየት ጋር ያሳያል፡፡ 40 ደቂቃ የሚወስደው ፊልም የተዘጋጀው በሰላም ኢትዮጵያ ነው፡፡

  የሰላም ኢትዮጵያ የኢቨንትና ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ አስተባባሪ አቶ ሲሳይ መንግሥቴ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ ፊልሙን ለማጠናቀቅ ሦስት ወር ፈጅቷል፡፡ ፊልሙ ሰላም ኢትዮጵያ ከሚያሰናዳቸው መርሐ ግብሮች አንዱ በሆነው የባህል ፎረም ይካተታል፡፡ ዳዊት ከሙዚቀኛነት ጎን ለጎን የሙዚቀኞች ማኅበርን በመምራት  ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከታቸው ለዘጋቢ ፊልም እንደመረጧቸው ተናግሯል፡፡

  ከ2,000 በላይ ሙዚቃዎችን ያቀናበሩት ዳዊት፣ ከልጅነታቸው አንስቶ እስከ ዛሬ ያሳለፉት ሕይወት ላይ ያተኮረው ፊልም ለዕይታ ሲበቃ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ሲሳይ ገልጿል፡፡ የመጀመሪያው የሙዚቀኛውን ተሞክሮ በመመርኮዝ ወጣት ሙዚቀኞችን ማስተማር ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዙሪያ ለሚካሄዱ ውይይቶች መነሻም ይሆናል፡፡ ‹‹ከሙዚቀኛው ሕይወት ውጣ ውረድ ትምህርት የሚወሰዱና ሙዚቃዎቻቸው የሚያነሳሷቸው ይኖራሉ፤›› ሲል ተናግሯል፡፡

  እሱ እንደገለጸው፣ ሙዚቀኛው በሕይወት ሳሉ ለአስተዋጽኦቸው ምሥጋና ማቅረብ ፊልሙ ከተሠራበት ዓላማ አንዱ ነው፡፡ ፊልሙ ለስነዳ እንደሚጠቅም ለጥናትና ምርምር መነሻ እንደሚሆንም እክሏል፡፡ ‹‹የሙዚቀኛው ታላላቅ ሥራዎች መሰነዳቸው ለሙዚቀኛውም የታሪክ መዝገብ ነው፤›› ብሏል፡፡

  አስተያየታቸውን ለሪፖርተር ከሰጡ የፊልሙ አዘጋጆች አንዱ ‹‹ፊልሙ ሙዚቀኛው በሕይወት ሳሉ ለአስተዋጽኦአቸው እንዲመሰገኑና ሥራዎቻቸውን ሕዝቡ በጥልቀት እንዲያውቅ መንገድ ይከፍታል፤›› ብሏል፡፡ ፊልሙ ከአራት አሠርታት በላይ ለኢትዮጰያ ዘመናዊ ሙዚቃ ያበረከቱትን እንደሚያንፀባርቅ ገልጿል፡፡

  ‹‹በተለይ ሮሃ ባንድ ውስጥ ከ200 አልበም በላይ ሠርተዋል፡፡ የበርካታ እውቅ ሙዚቀኞች ሥራ ላይ አሻራቸው አርፏል፤›› በማለት ተናግሯል፡፡ ጥላሁን ገሠሠ፣ መሐሙድ አህመድ፣ ምኒሊክ ወስናቸው፣ መልካሙ ተበጀ፣ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሐመልማል አባተ፣ ኩኩ ሰብስቤና ሙሉቀን መለሰ ጥቂቱ ናቸው፡፡ ከዳዊት ቤተሰቦች አብዛኞቹ ሙዚቀኞች መሆናቸውን በማጣቀስ፣ ‹‹አሁንም አሻራቸውን እያሳረፉ ነው፤›› ብሏል፡፡ ከዳዊት ልጆች አንዱ ናሆም ዳዊት ይጠቀሳል፡፡

  ፊልሙ ግንቦት 19፣ 2007 ዓ.ም. ከተመረቀ በኋላ በተለያየ መንገድ ለሕዝብ እንደሚደርስ፣ በምርቃቱ እለት ፊልሙ በነፃ እንደሚታደልና በማኅበረሰብ ድረ ገጽና በቴሌቪዥን እንዲተላለፍ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

  ፊልሙ ለሰላም ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዘጋቢ ፊልም ነው፡፡ ሲሳይ እንደተናገረው፣ በሙዚቃው ዘርፍ ላሉ ባለድርሻ አካላት የውይይት መነሻ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በምርቃቱ ዕለት አንጋፋና ወጣት ሙዚቀኞች፣ የሙዚቃ ተማሪዎችና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ በተለይም ከሙዚቀኛው ጋር የሠሩ ባለሙያዎች መርሐ ግብሩን እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡ በዕለቱ ከሚኖረው ውይይት የሚገኘው ግብዓት በቀጣይ ለሚሠሩ መሰል ዘጋቢ ፊልሞች መነሻ እንደሚሆን አመላክቷል፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...