Tuesday, February 27, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስትር

[ክቡር ሚኒስትሩ ከወዳጃቸው ጋር ቢሯቸው ተገናኙ]

 • ኳስ ይወዳሉ ክቡር ሚኒስትር?
 • ኳስ እኮ ሁለተኛ ሃይማኖቴ ነው፡፡
 • የመጀመሪያ ሃይማኖትዎ ምንድነው?
 • አብዮታዊ ዲሞክራሲ፡፡
 • እሱ ሃይማኖት መሆኑን አላውቅም ነበር፡፡
 • ለእኔ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከሃይማኖትም በላይ ነው፡፡
 • ከሃይማኖት በላይ ደግሞ ምን ሊሆን ነው?
 • ለእኔ ሕይወቴ ነው፣ ሁሉ ነገሬ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ሕይወትዎ ይቀያየራል ማለት ነው?
 • ምን ማለትህ ነው?
 • ያኔ ጫካ እያላችሁ እኮ ሶሻሊዝም ሕይወቴ ነው ይሉኝ ነበር፡፡
 • የማይቀየር ነገር ምን አለ ብለህ ነው?
 • ለነገሩ እውነትዎትን ነው፤ ይኸው ኢትዮጵያ ራስዋ ተቀይራለች አይደል?
 • እሱን እኮ ነው የምልህ? ሁሌም መገላበጥ ጥሩ ነው፡፡
 • ያልተገለበጠ ያራል አይደል ተረቱ?
 • ካልተገላበጥክ እኮ ትገለበጣለህ፡፡
 • ጊዜው የመገለባበጥ ነው እያሉኝ ነው?
 • ጊዜውማ የኢሕአዴግ ነው፡፡
 • የሻምፒየንስ ሊግን ይከታተላሉ?
 • ስነግርህ ከፖለቲካ ቀጥሎ እግር ኳስ ነው የምወደው፡፡
 • ለነገሩ ኳስና ፖለቲካ እኮ ተመሳሳይ ናቸው፡፡
 • እንዴት ሆኖ?
 • በመጀመሪያ ሁለቱም ጨዋታ ናቸው፡፡
 • አልገባኝም?
 • አንደኛው የኳስ ጨዋታ ነው፤ ሌላኛው የፖለቲካ ጨዋታ ነው፡፡
 • እሺ፡፡
 • ሁለቱም ጨዋታ ላይ ደግሞ ተፎካካሪ አካላት አሉ፡፡
 • እሱስ ልክ ነው፡፡
 • በሁለቱም ጨዋታ ላይ ዳኛ አለ፡፡
 • እርግጥ ነው፡፡
 • ታዛቢም አለ፡፡
 • ሌላስ?
 • ሁለቱንም ጨዋታዎች ሕዝብ ሁሌም በጉጉት ይጠብቃቸዋል፡፡
 • ልክ ብለሃል፡፡
 • ለማንኛውም የማን ደጋፊ ነዎት?
 • እኔ ደጋፊ ሳልሆን ተወዳዳሪ ነኝ፡፡
 • የሻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ ላይ ማለቴ ነው፡፡
 • ለባርሳ ነኛ፡፡
 • ለማን አሉኝ?
 • ለገዢው ቡድን፡፡
 • ማነው ገዢው?
 • አውራው ነዋ፡፡
 • እኮ ማነው አውራው?
 • ባርሳ አልኩህ፡፡
 • እኔ ግን ተፎካካሪው ቢያሸንፍ ደስ ይለኛል፡፡
 • ተቃዋሚዎች?
 • የለም ጁቬንትስ ማለቴ ነው፡፡
 • አውራው እንደሚያሸንፍማ የተረጋገጠ ነው፡፡
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • በርካታ ቡድኖችን አሸንፎ ነው እዚህ የደረሰው፡፡
 • ተፎካካሪውም ቢሆን እኮ ቀላል አይደለም፡፡
 • ምን እያልከኝ ነው?
 • ተፎካካሪው አካል በርካታ መንገዶችን አልፎ ነው እዚህ የደረሰው፡፡
 • እና ተቃዋሚዎች ገዢውን ፓርቲ ያሸንፋሉ እያልክ ነው?
 • የለም እኔ ስለጁቬንትስ ነው እያወራሁ ያለሁት፡፡
 • እህህህ… እሱንማ ነገርኩህ ዋንጫው የባርሳ ነው፡፡
 • የማን ነው አሉኝ?
 • የገዢው፡፡
 • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
 • ዳኞች ራሱ ለእርሱ ነው የሚያግዙት፡፡
 • ለምን ያግዛሉ?
 • የዛሬ ስድስት ዓመት ቼልሲ ከባርሴሎና ጋር ለዋንጫ ለማለፍ የተጫወቱት ጨዋታ ትዝ ይልሃል?
 • እስቲ ያስታውሱኝ?
 • በዚያ ጨዋታ ቼልሲ ንፁህ አራት የፍጹም ቅጣት ምት አልተሰጠውም፡፡
 • አዎን ትዝ አለኝ፡፡
 • ለምን እንደዚያ እንደሆነ ታውቃለህ?
 • አላውቅም፡፡
 • ከቼልሲ ይልቅ ባርሴሎና ቢያልፍ ትልቅ ትርፍ ከቴሌቪዥን ማስታወቂያ ስለሚገኝ ነው፡፡
 • ስለዚህ ዳኛዎችም ለባርሳ ይደግፋሉ እያሉኝ ነው?
 • እንዴታ ገዢውን ማን የማይደግፍ አለ?
 • ሁሌም ግን እንደዚህ አይመስለኝም፡፡
 • እስቲ አንድ ምሳሌ ስጠኝ?
 • የዛሬ አሥር ዓመቱ የዋንጫ ጨዋታ ትዝ ይልዎታል?
 • መቼ የተደረገው?
 • በ97 አልኩዎት፡፡
 • የ97 ምርጫን ነው?
 • የለም የለም፣ በዚያ ዓመት የተካሄደው የሻምፒየንስ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ፡፡
 • እስቲ አስታውሰኝ፡፡
 • ለዋንጫ የደረሱት ሊቨርፑልና ኤሲ ሚላን ነበሩ፡፡
 • እሺ፡፡
 • ለኤሲ ሚላን ከፍተኛ ግምት ሲሰጠው ተፎካካሪው ግን አነስተኛ ግምት ነበር የተሰጠው፡፡
 • ከዚያስ?
 • ከዚያማ ኤሲ ሚላን በጨዋታው ሦስት ለዜሮ ሲመራ ቆይቶ ኋላ ላይ ውጤቱ ተቀየረ፡፡
 • ውጤቱ ምን ሆነ?
 • ያልተጠበቀው ተፎካካሪ አሸነፈ፡፡
 • በ97 ምርጫ ተፎካካሪዎቻችን መቼ አሸነፉ?
 • ኧረ እኔ ኳሱን ነው ያልኩዎት፡፡
 • እ…
 • ለነገሩ በኢትዮጵያ ምርጫም ቢሆን ያልተጠበቀ ነገር ነበር የተከሰተው፡፡
 • እንዴት?
 • ያው ተቃዋሚዎች በርካታ የፓርላማ መቀመጫዎችን አሸንፈው ነበራ፡፡
 • ቢሆንም ግን አሸናፊው ፓርቲ የእኛው ገዢ ፓርቲ ነበር፡፡
 • ዋናው ነጥቤ እሱ አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምንድነው ታዲያ?
 • ጨዋታው ፌርና ክሬደብል ሊሆን ይገባዋል፡፡
 • ለምን?
 • ፌርና ክሬደብል ካልሆነ ተወዳጅም አይሆንም፡፡
 • የፖለቲካ ጨዋታውን ነው የምትለኝ?
 • የፖለቲካውም ሆነ የኳሱ ጨዋታ፡፡
 • ስለዚህ ዳኛዎቹ ነፃና ገለልተኛ መሆን አለባቸው እያልከኝ ነው?
 • በሚገባ ክቡር ሚኒስትር፤ ምክንያቱም ዳኛዎቹን የሚዳኝ ሌላ ዳኛ እኮ አለ፡፡
 • ማነው እሱ?
 • ሕዝቡ፡፡
 • የትኛው ሕዝብ?
 • ተመልካቹ ነዋ፡፡
 • አሃ… ለካ ዳኛዎቹ ሜዳ ላይ ቢዳኙም፣ ሕዝቡ በየቤቱ ዳኛ ነው፡፡
 • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ስለዚህ የፖለቲካ ጨዋታው ዳኛም ነፃና ገለልተኛ ሊሆን ይገባል እያልከኝ ነው?
 • ዳኛው ነፃና ገለልተኛ ካልሆነማ፣ የጨዋታው ተዓማኒነት ይቀንሳል፡፡
 • ወይ ጣጣ፡፡
 • በዚያ ላይም ታዛቢም አለ፡፡
 • የምን ታዛቢ?
 • አራተኛ ዳኛው ነዋ፡፡
 • የእሱ ሥራ ደግሞ ምንድነው?
 • ጨዋታውን መታዘብ፡፡
 • ታዝቦ ሲያበቃ ምን ያደርጋል?
 • የእሱ ሪፖርት ለጨዋታው ተቀባይነት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
 • በደንብ ባይታዘብስ?
 • እሱንም ሕዝቡ ይታዘበዋል፡፡
 • ስለዚህ የፖለቲካ ጨዋታውም ታዛቢ ያስፈልገዋላ?
 • ለዚህኛውም ጨዋታ ተዓማኒነት የታዛቢው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
 • ወይ ጉድ፡፡
 • ስለዚህ ለጨዋታው ተዓማኒነትና ተቀባይነት ገዢውም፣ ተፎካካሪውም፣ ዳኛውም፣ ታዛቢውም በሚገባ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡
 • ልክ ብለሃል፡፡

 

[ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸው ጋ ደወሉ] 

 • አንተ ኳስና ፖለቲካ አንድ ዓይነት ናቸው እንዴ?
 • በርካታ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡
 • ወይ ጉድ፡፡
 • ለምን ጠየቁኝ?
 • አይ ይኼንን እንደምታውቅ ለማወቅ ብዬ ነው፡፡
 • እና ለዋንጫው ጨዋታ ተዘጋጅተዋል?
 • አዎን ግን…
 • የምን ግን ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ለዚህ ጨዋታ እኮ ሕዝቡ ወሳኝ ነው፡፡
 • እንዴታ ክቡር ሚኒስትር? የጨዋታው ፈራጅ ሕዝቡ ነው፡፡
 • ታዲያ ለዚህ ሕዝብ ምን እናድርግለት?
 • እንግዲህ ያደረግነውን ነገር ሁሉ እስከዛሬ አስታውቀነዋል፡፡
 • አሁን ለሕዝቡ የምንመርቅለት ፕሮጀክት የለም?
 • ክቡር ሚኒስትር፣ ሁሉንም ፕሮጀክቶች አስመርቀናል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ቦታ ላይ ደግመን ራሱ የመረቅናቸው ፕሮጀክቶች አሉ፡፡
 • አሁን ይኼ ሕዝብ ደግመን ደጋግመን ብናስመርቅለትስ ምን ይለዋል?
 • ከዚያም አልፈን ዕቅድ ላይ ለሌለ ፕሮጀክት ራሱ የመሠረት ድንጋይ ጥለናል፡፡
 • ኧረ ይኼ ሕዝብ ሲያንሰው ነው፡፡
 • እንዳይታዘበን ግን መጠንቀቅ አለብን፡፡
 • እንዳይታዘበን ነው እኮ የሚመረቅ ነገር ፈልግ የምልህ?
 • ምን ተሻለ ታዲያ?
 • ለምን ተማሪዎችን አናስመርቅም?
 • የትምህርት ዘመኑ ገና ነዋ፡፡
 • ወይ ጣጣ፡፡

[ክቡር ሚኒስትሩ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸውን አገኟቸው] 

 • ምነው ፊትህ ጠቋቆረ?
 • እንዴት አይጠቋቁር?
 • በቃ ምርጫ ሲደርስ ቀለምህ ራሱ ይቀያየራል?
 • እንዴት አይቀያየር?
 • እኮ ምን ሆነሃል?
 • ለካ ለዚህ ምርጫ ሕዝቡ ወሳኝ ነው?
 • ይኼን ሳታውቅ ነው እስከዛሬ ፖለቲከኛ የነበርከው?
 • አሁን ነው በእጅጉ የተገለጠልኝ፡፡
 • ከራስህ በፊት ሁሌም ሕዝቡን አስቀድም የምልህ ለዚህ ነው፡፡
 • አሁን እኮ እንዳይቀድመኝ ፈርቼ ነው፡፡
 • ሕዝቡማ ከቀደማችሁ ቆየ፡፡
 • ሳትቀደም ቅደም አሉ፡፡
 • ምን ልታደርግ ነው?
 • እየፈለግኩኝ ነው፡፡
 • ምን?

[የክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ጠራ]  

 • አቤት፡፡
 • አዎ ነኝ፡፡
 • ምን አልከኝ?
 • አለቀ?
 • አዎን እገኛለሁ፡፡
 • ታንኪው!

[ክቡር ሚኒስትሩ ስልካቸውን ዘግተው ከሚስታቸው ጋር ማውራት ቀጠሉ] 

 • ምነው ደስ አለህ?
 • ተገኘ፡፡
 • ማነው የደወለልህ?
 • ያ የመኖሪያ ቤት የሚሠራው ዘመዴ ነው፡፡
 • ምን አለህ ታዲያ?
 • የመኖሪያ ቤቱን ጨረሰው፡፡
 • በጣም ደስ ይላል፡፡
 • ምን ደስ ይላል ብቻ፣ ገላገለኝ እንጂ፡፡
 • እንዴት?
 • እኔም ቤት አገኘኋ፡፡
 • የምን ቤት?
 • የሚመረቅ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...