Saturday, September 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጤናው ዘርፍ አቅጣጫ ጠቋሚ

የጤናው ዘርፍ አቅጣጫ ጠቋሚ

ቀን:

በአገሪቱ የጤና ዘርፍ አዎንታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሎ በብዙዎች የታመነበት የመጀመሪያው የጤና አገልግሎት ማውጫ መታተም ይፋ የሆነው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ 554 ገጾች ያለውንና የአገሪቱ የመንግሥትና የግል እንዲሁም የሌሎችን የጤና ነክ የጤና ተቋማትን መረጃ የያዘው ማውጫን በሚመለከት ማውጫውን ካዘጋጁትና የኢትዮጵያ የግሉ ጤና ዘርፍ ሐኪሞች ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ ጋር ምሕረት አስቻለው አጭር ቆይታ አድርጋለች፡፡

ሪፖርተር፡- የማውጫው ዝግጅት ምን ይመስል ነበር?

ዶ/ር ወንድወሰን፡- በአገሪቱ ባሉ 850 ወረዳዎች ላይ ዳሰሳ ተሠርቶ ነው መረጃ የተሰበሰበው፡፡ መረጃዎቹን የማረጋገጥ ሥራ የተሠራው ደግሞ ባለፈው ዓመት ሲሆን፣ የማረጋገጥ ሥራውም 45 ቀናት ያህል ወስዷል፡፡ አጠቃላይ የማውጫው ዝግጅት ሁለት ዓመት ከአራት ወር ገደማ ፈጅቷል፡፡

ሪፖርተር፡- ጥቂት የማይባሉ የግል የጤና ተቋማት አድራሻቸውን በየጊዜው ይቀያይራሉ፡፡ ይህ ችግር አይሆንም?

ዶ/ር ወንድወሰን፡- በማውጫው 170 የግል ተቋማትና የሦስት መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት መረጃ ተካትቷል፡፡ በግል ተቋማት በኩል አድራሻ የመቀያየር ነገር አለ፡፡ ትክክል ነው፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግ ከማውጫው ላይ ያሰፈርነው የሞባይል ስልኮችን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የማውጫው ጠቀሜታ እስከምን ድረስ ይሆናል?

ዶ/ር ወንድወሰን፡- ለግለሰቦች፣ ለሕክምና ባለሙያዎች፣ በዘርፉ ለተሰማሩ ቢዝነሶች ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ አንድ ዶክተር ታካሚን ለአንድ ዓይነት ሕክምና የት ልላከው ብሎ መቸገር አይኖርበትም፡፡ ማውጫው ሪፈራልን ያሳልጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በሌላ በኩል ለምሳሌ 380 የሕክምና ዕቃ አስመጭዎች አሉ፡፡ ዕቃ ማስመጣት የሚፈልጉ ረጅም ጊዜ ወስደው እያንዳንዱ ጋር ከሚዞሩ የሚፈልጉትን መረጃ በቀላሉ በስልክ እየደወሉ በመጠያየቅ ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ጤና ነክ የሆኑ ድርጅቶችን የሚመለከት መረጃም በማውጫው ላይ አለ?

ዶ/ር ወንድወሰን፡- አዎ፡፡ ምንም እንኳ የብዙዎቹ ሥራ በጅምር ላይ ቢሆንም ሃያ የሚሆኑ ለየት ያለ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት መረጃም ተካትቷል፡፡ ሰው ሠራሽ እግርና እጅ የሚሠሩ፣ አስከሬን የሚያቆዩ፣ ተጥለው የተገኙ ሕፃናትን የሚቀበሉና የአዕምሮ ዘገምተኛ ሕፃናት ማዕከላት በዚህ ዘርፍ በምሳሌነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር፡- የማውጫው ዝግጅት አጠቃላይ ወጪስ ምን ያህል ነው?

ዶ/ር ወንድወሰን፡- ሦስት ሚሊዮን ብር አስወጥቷል፡፡ መጀመሪያ ማውጫው ባለ 960 ገጽ፣ ኪሎውም ሦስት ኪሎ ተኩል ነበር፡፡ ለማሳተም አስበን የነበረው አገር ውስጥ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ያሳተምነው ቻይና ነው፡፡ እዚያ በመታተሙ ጥራቱ እንዲጨምር ክብደቱም ወደ አንድ ኪሎ ተኩል እንዲቀንስ አስችሏል፡፡ አሁን የታተመው ሃያ ሺሕ ያህል ሲሆን እስከ ሰኔ 2007 ዓ.ም. በማውጫው ለተካተቱ ጤና ተቋማት በሙሉ በነፃ ይሰራጫል፡፡

ሪፖርተር፡- ማውጫውን በማዘጋጀት ሒደት ትልቁ ተግዳሮት ምን ነበር?

ዶ/ር ወንድወሰን፡- ብዙ ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡ ሆኖም ገንዘብ ትልቁን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ሥራውም በራሱ አድካሚ ነበር፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...