Thursday, June 8, 2023

ምርጫ 2007

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

እሑድ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ሒደት በጊዜ ሰሌዳው መሠረት፣ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚነት በሚካሄደው አምስተኛ ጠቅላላ ምርጫ፣ ከ36.8 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተመዝግበው ድምፅ እንደሚሰጡ ሲጠበቅ፣ በመላ አገሪቱ 46 ሺሕ ምርጫ ጣቢያዎች መራጮችን ለማስተናገድ ተዘጋጅተዋል፡፡

በምርጫ ቦርድ መረጃ መሠረት እስካሁን ድረስ 319 ሚሊዮን ብር የወጣበት የዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ በርካታ ክስተቶች የታዩበት ሲሆን፣ በምርጫው ለመወዳደር ተመዝግበው የምርጫ ምልክቶች ከወሰዱ 58 ፓርቲዎች መካከል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) እና ሰማያዊ ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ ጋር ሲነታረኩ ከርመዋል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ በመጨረሻው ምዕራፍ በደቡብ ክልል በካፋ ዞን፣ በጊምቦ የምርጫ ክልል በግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስና በደኢሕዴግ/ኢሕአዴግ ዕጩ ዶ/ር መብራቱ ገብረ ማርያም ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ምርጫው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አስገድዷል፡፡ በገጽ ፖለቲካ ገጽ ላይ የተስተናገደው የነዓምን አሸናፊ ዘገባ ከምርጫ 2007 ጋር የተገናኙ በርካታ ክስተቶችን ያስቃኛል ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -