Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ለየት ያሉ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ለየት ያሉ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ

ቀን:

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከዚህ በፊት ከነበሩት ለየት ያሉ ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተጠቆመ፡፡

የብአዴን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለምነው መኮንን፣ የክልሉን ሕዝብ ችግሮች በዘላቂነት ሊፈታ የሚያስችልና ከዚህ በፊት ይተላለፉ ከነበሩት ለየት ያሉና ጠንካራ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደተጀመረ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ በክልሉ በተለይም በወልዲያ፣ በመርሳ፣ በቆቦና በሌሎች ከተሞች ተከስቶ በነበረው ግጭት ስብሰባው ተቋርጦ ነበር፡፡ ተቋርጦ የነበረው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ባለፈው ሳምንት እንደተጀመረ አቶ ዓለምነው ጠቁመው፣ በስብሰባው ማጠቃላይ ላይ ለየት ያሉና የክልሉን ሕዝብ ጥያቄ በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉ የውሳኔ ሐሳቦች ይተላለፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡

ለየት ያሉ የውሳኔ ሐሳቦች ይተላለፋሉ ሲባል ምን ዓይነት ጉዳዮችን ሊያካትቱ ይችላሉ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ዓለምነው በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹አሁን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ዋነኛው አጀንዳ ላይ ውይይት እያደረጉ ነው፡፡ ስለዚህ ውይይቱ ሲጠናቀቅ የሚተላለፉ ውሳኔዎች ይታወቃሉ፤›› ብለዋል፡፡ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ያደረገውን ስብሰባ አጠናቅቆ ወደ ሂስና ግለሂስ መሸጋገሩን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡ ሂስና ግለሂሱ ሲጠናቀቅም ዕርምጃ የሚወሰድባቸውና ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የሚታገዱ ሰዎች ከመኖራቸውም በላይ፣ ጠንካራ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ዓለምነው ውሳኔዎች የተለዩና ጠንካራ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢያረጋግጡም፣ የክልሉን መንግሥት በመምራት ላይ ባሉ ከፍተኛ ኃላፊዎች ላይ ዕርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ የጊዜ ገደብ እንዳልተቀመጠለትና የሚጠናቀቅበት ቀን በውል እንደማይታወቅ አቶ ዓለምነው ገልጸው፣ ‹‹የውይይቱ ባህሪ የሚጠናቀቅበትን የጊዜ ገደብ ይወስናል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ወደዚህ ስብሰባ ስንገባ ግን ጠንካራና ለየት ያሉ ውሳኔዎች መተላለፍ አለባቸው በሚል አቋም ነው፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ስብሰባ ሲጀምር በወልዲያ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ዜጎች ሕይወታቸው መጥፋቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በወልዲያ ከተማ በወጣቶችና በፀጥታ አካላት መካከል ግጭት ተቀስቅሶ ነበር፡፡ ግጭቱ ወደ ሌሎች ከተሞች ተስፋፍቶ በአጠቃላይ የአሥራ አምስት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ አይዘነጋም፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደጠቆሙት በስብሰው ማጠቃለያ ላይ በከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች ላይ ዕርምጃ ይወሰዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...