የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዞን 9 ጦማሪዎች ክስ እንዲቋረጥና እንዲለቀቁ ወሰነ፡፡ ክሳቸው እንዲቋረጥ የተወሰነላቸው ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ኃይሉና አጥናፍ ብርሃኔ ሲሆኑ፣ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ነበር ክስ የተመሠረተባቸው፡፡ ተከሳሾቹ ዛሬ የፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበራቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤት ሲደርሱ ክሳቸው እንደተቋረጠ ተነግሯቸው ወደየቤታቸው እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ቀደም ከፊል የዞን 9 ጦማሪዎች በነፃ መሰናበታቸው ይታወሳል፡፡ በተያያዘ ዜና እስክንድር ነጋና አንዷለም አራጌን ጨምሮ 746 ተከሳሾች ክስ ተቋርጦ እንዲፈቱ በተወሰነው መሠረት ሁሉም እስረኞች ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ከማረሚያ ቤት እየወጡ ነው፡፡