Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ይፋ ሆነ

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ይፋ ሆነ

ቀን:

የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን ይፋ አደረገ፡፡ ዕውቅናው ጽሕፈት ቤቱ የሚሰጣቸው ማንኛውንም ዓይነት አክሬዲቴሽን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው፡፡ ዕውቅናውን ያገኘው በፍተሻ ላቦራቶሪ ‹‹iso 17025›› እና በሕክምና ላቦራቶሪ ‹‹iso 15189›› ዘርፎች ነው፡፡ በዓለም የሚገኙ የአክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤቶች የሚተዳደሩበትን ‹‹iso 17011›› ተግባራዊ ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ዕውቅናው የተሰጠው፡፡

ጽሕፈት ቤቱ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከማግኘቱ በፊት በተለያየ ዘርፍ ለተቋማት ይሰጥ የነበረው ዕውቅና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት አልነበረውም፡፡ ስለዚህም በአገር ውስጥ የሚደረገው ማንኛውም የሕክምና ላቦራቶሪ ከአገር ሲወጣ በድጋሚ እንዲፈተሸ ይደረግ ነበር፡፡ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱ ግን በድጋሚ የሚደረገውን ምርመራ የሚያስቀር መሆኑ ተገልጿል፡፡

‹‹ለሦስት ዓመታት ለፍተን ነው ዕውቅናውን ያገኘነው፡፡ ከግብፅ፣ ከሜክሲኮና ከሞሪሺየስ የተውጣጡ ባለሙያዎች ጽሕፈት ቤቱ ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን፣ ብቁ ባለሙያዎች እንዳሉት እንዲሁም ዕውቅና ባገኘባቸው በሕክምና ላቦራቶሪና በፍተሻ ላቦራቶሪ ዕውቅና የሰጣቸው ተቋማት ድረስ በግንባር በመሄድ ግምገማ አድርገዋል፤›› ያሉት የጽሕፈት ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ንጉሤ ክብሩ ናቸው፡፡  

አንድ አገር የዓለም አቀፍ ላቦራቶሪ አክሬዲቴሽን ትብብር አባል ሲሆን፣ ከአገሩ የሚወጣ የላቦራቶሪ ውጤት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሁሉም ቦታ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ያገኘው ዕውቅናም የዚህ ዓለም አቀፍ ትብብር አካል የሚያደርገው ነው፡፡ ‹‹በኢንስፔክሽን ዘርፍ ገና እየሠራን ነው፡፡ እስካሁን ለአራት ድርጅቶች ብቻ ነው ዕውቅና የሰጠነው፡፡ አንዱ የምንገመገምበት መስፈርትም የምንሰጠው አገልግሎት ነው፡፡ ለዚህም በቂ ተጠቃሚ ሊኖር ይገባል፤›› ያሉት አቶ ንጉሤ ተቋማት ዕውቅና ማግኘት የሚያስገኘውን ጥቅም ተረድተው ወደ ጽሕፈት ቤቱ መሄድ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

‹‹ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታችን ምርቶችን ለውጭ ገበያ ለሚልኩ አካላት ትልቅ ነገር ነው፡፡ የተቋቋምንበት ዋና ዓላማም ወደ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ኖሯቸው፣ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲቀርቡ ለማድረግ ነው፤›› ያሉት የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍሥሐ ናቸው፡፡ አክለውም ማኅበረሰቡ የሚገለገልበትን የሕክምና መስጫ ዕውቅና እንዳለው ማረጋገጥ እንዳለበት፣ የሕክምና ባለሙያዎችም ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በ2003 ዓ.ም. የተቋቋመው ጽሕፈት ቤቱ እስካሁን በኢንስፔክሽን፣ በሕክምና የፍተሸ ላቦራቶሪ፣ በሕክምና ላቦራቶሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ተቋማት ዕውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በድምሩ እስካሁን 30 ለሚሆኑ ተቋማት ዕውቅና ሰጥቷል፡፡ በኢንስፔክሽን ዘርፍ ዕውቅና ማግኘት የቻሉ በግብርን ኢንስፔክሽን ዘርፍ የተሰማሩ አራት ተቋማት ብቻ ናቸው፡፡ 16 ተቋማት በፍተሻ ላቦራቶሪ፣ 11 ደግሞ በሕክምና ላቦራቶሪ ዕውቅና ማግኘት ችለዋል፡፡ አጠቃላይ በሕክምና ላቦራቶሪ በየዘርፉ የተሰጡት ዕውቅናዎች 28 ደርሰዋል፡፡ አንዳንዶቹ ተቋማት በተለያዩ ዘርፎች ዕውቅና እንደተሰጣቸው የሚናገሩት በጽሕፈት ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ንጉሤ ክብሩ ናቸው፡፡ አዳማ ጄኔራል ሆስፒታልን ለአብነት ያህል ያነሱት አቶ ክብሩ ሆስፒታሉ እንደ ሂማቶሎጂ፣ ኢሚውኖሎጂ ባሉ አራት ዘርፎች አክሬዲቴሽን እንዳለው ገልፀዋል፡፡ በሁለቱ ዘርፎች ዕውቅና ለማግኘት ያመለከቱ 11 ተቋማት ጉዳያቸው እየታየላቸው ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...