በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ረዥሙና 55 ቀኖችን የሚይዘው ዐቢይ ጾም (ሑዳዴ) የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በምዕመናኑ ዘንድ ተጀምሯል፡፡ ዋዜማው እንደሁሌው በቅበላነቱ በሥጋና በወተት በቅቤም ተዋጽዖዎች ታጅቦ አልፏል፡፡ በሥነ ቃል የተመዘገበው፣
‹‹ጀግናው ዐቢይ ጾም ቢታይ ብቅ ብሎ
ቅቤ ፈረጠጠ ሀገር ድስቱን ጥሎ›› ሰኞ ዕለት ሲሰማ ነበር፡፡ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ከታዩት ግብይቶች አንዱ በፎቶው የሚታየው ነው፡፡
- ሔኖክ መደብር