Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤትም ሆነ ሒደት እንደማይቀበል አስታወቀ

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤትም ሆነ ሒደት እንደማይቀበል አስታወቀ

ቀን:

በዘንድሮ አምስተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ለመጀመርያ ጊዜ ተካፋይ የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደውን ምርጫ ውጤትም ሆነ ሒደት እንደማይቀበል አስታወቀ፡፡

የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ስለሺ ፈይሳና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በፓርቲው ጽሕፈት ቤት ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፣ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት ያስታወቁት፡፡

‹‹ነፃነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው›› በሚል ርዕስ በሰጠው መግለጫ ፓርቲው እንዳስታወቀው፣ የ2 007ን ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን በዚህች አገር ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ቡድንም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ ግልጽ ማድረጉን፣ በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የተካሄደው ምርጫ ውጤትም ተቀባይነት የለውም ሲል በመግለጫው አስታውቋል፡፡

‹‹በሕገወጥ የአፈና ሥርዓት የተካሄደው የ2007 ዓ.ም. ጠቅላላ ምርጫ የሚያመለክተው ኢትዮጵያ አሁንም ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ልታካሂድ ቀርቶ፣ በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት ምርጫዎች ጋር እንኳን ሊወዳደር የሚይችል እጅግ ኢ-ፍትሐዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሒደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፤›› በማለት ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ከጋዜጠኞች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን፣ አመራሮቹም ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከተነሱ ጥያቄዎችም መካከል ቁጥራቸው ካልተገለጹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮች የማሸነፍ ዕድል ይኖረናል የሚል ግምት አላችሁ ወይ የሚል የነበረ ሲሆን፣ የፓርቲው ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ይልቃል፣ ‹‹ያልተገለጹ መቀመጫዎችን ለማሸነፍ ምንም ተስፋ የለንም፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው፣ ‹‹ፓርቲያችን በዚህ አፈናና ጭቆና ውስጥ ከሕዝብ ለተሰጠው ክብር ያመሰግናል፡፡ በምርጫ ሒደቱ የተደበደባችሁና የተሰደዳችሁ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች፣ ፓርቲያችን ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተዓማኒ፣ ተወዳጅና ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን እናንተ ላይ የደረሰው መከራና በደል ትልቁን ድጋፍ ይወስዳልና ክብርና ምሥጋና ይገባችኋል፤›› ብሏል፡፡

‹‹የዜጎች ነፃነት ሳይከበር ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ሊደረግ ስለማይችል አሁንም ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብታችን እስከሚከበሩ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነፃነት ትግል ኢትዮጵያዊያን ከጎኑ እንዲቆሙ ይጠይቃል፤›› በማለት የፓርቲው መግለጫው ያትታል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ በበርካታ የምርጫ ክልሎች ከኢሕአዴግ በመቀጠል የመራጮችን ድምፅ ማግኘቱን፣ ከተለጠፉት የውጤት ማሳወቂያ ዝርዝሮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...