ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነትና ከጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን አስታወቁ፡፡ ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንደሚያገኝም እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ነገር ግን መልቀቂያቸው በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና በደኢሕዴን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተቀባይነት ማግኘቱን ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ከሥልጣን የሚለቁበትን ምክንያት ሲያስረዱ፣ አገሪቱ ያለችበት ሁኔታ አሳሳቤ ስለሆነ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ለማድረግ እንዲረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ወደፊትም በፓርቲያቸው ውስጥ ሆነው የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ አክለዋል፡፡