Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍርፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

ቀን:

‹‹ያለንበት ዘመን አዳዲስ ሐሳቦች የሚፈልቁበትና አዳዲስ አመራር የሚፈልግ በመሆኑ፣ የጆሴፍ ሴፕ ብላተር በፊፋ ፕሬዚዳንትነት መቀጠል ተቀባይነት የለውም፡፡››

ዝነኛው የእግር ኳስ ተጫዋችና አሠልጣኝ ዮሐን ክሩፍ በቴሌግራፍ ጋዜጣ ዓምዱ ላይ ካሰፈረው የተወሰደ፡፡ የዓለም እግር ኳስ የበላይ የሆነው ፊፋ በሙስና ምክንያት ብዙ እየተባለ ባለበትና የተወሰኑ አመራሮችም በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ፣ ፕሬዚዳንቱ ሴፕ ብላተር ለአምስተኛ ጊዜ መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ ሆላንዳዊው የእግር ኳስ ባለታሪክ ክሩፍ ግን ብላተርም ይበቃቸዋል፣ የፊፋ ሲስተምም ተብጠርጥሮ መመርመር አለበት ብሏል፡፡ ብላተር እ.ኤ.አ. ከ1998 ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፕሬዚዳንትነት መምራታቸውና ለመጪዎቹ አራት ዓመታት መመረጣቸው፣ የዘመኑን አስተሳሰብ አይወክልም ብሏል ክሩፍ፡፡ የቀረበው የሙስና ወንጀል እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን እንደማያውቅ የገለጸው ክሩፍ፣ በእንዲህ ዓይነቱ አሳሳቢ ጊዜ ግን ብላተርን በሥልጣን ላይ ማየት አያስፈልግም ብሏል፡፡ ለዚህ ደግሞ የአውሮፓ አገሮች አስፈላጊውን ዕርምጃ በኅብረት እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች በፊፋ ጉዳይ ላይ የተለያየ አቋም እያንፀባረቁ ሲሆን፣ የእንግሊዝ እግር ኳስ ማኅበር ግን ብላተር በአስቸኳይ ከሥልጣናቸው ካልወረዱ እያለ ነው፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታየው ዮሐን ክሩፍ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...

ማን ይቻለን?

በጠዋት የተሳፈርንበት ታክሲ ውስጥ በተከፈተው ሬዲዮ፣ ‹‹ይኼኛው ተራራ ያን...