Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትእበት ለቃሚው ጥንዚዛ

እበት ለቃሚው ጥንዚዛ

ቀን:

የእንስሳት እዳሪ ለእበት ለቃሚ ጥንዚዛዎች ብዙ ጥቅም ይሰጣል። ለምግብነት ይጠቀሙበታል እንዲሁም እንቁላላቸውን ይጥሉበታል። አንዳንድ ወንዴ ጥንዚዛዎች ደግሞ በርከት ያለ እዳሪ ሰብስበው እንስቷ ፊት በማቅረብ እሷን ለማማለል ይሞክራሉ። እዳሪው ትኩስ ከሆነ ሽሚያው በጣም የጦፈ ይሆናል። በአንድ ወቅት 16,000 ገደማ የሚሆኑ ጥንዚዛዎች በዝሆን ፋንዲያ ላይ ተረባርበው በሁለት ሰዓት ውስጥ ድራሹን ሲያጠፉት ተመራማሪዎች ተመልክተዋል።

አንዳንድ እበት ለቃሚ ጥንዚዛዎች ከግርግሩ ለማምለጥ ሲሉ እበቱን ካድቦለቦሉ በኋላ እያንከባለሉ ይወስዱታል፤ ከዚያም ለስላሳ በሆነ አፈር ውስጥ ይቀብሩታል። ጥንዚዛዎቹ ያድቦለቦሉትን እዳሪ እያንከባለሉ የሚወስዱት ቀጥ ያለ መስመር ተከትለው ነው፤ እንዲህ ማድረጋቸው ከአካባቢው ፈጥነው ለመራቅ ብሎም የያዙት እዳሪ በሌሎች ጥንዚዛዎች የመሰረቅ አጋጣሚውን ለመቀነስ ያስችላቸዋል።

ይሁን እንጂ እነዚህ እበት ለቃሚ ጥንዚዛዎች በተለይ ሌሊት ላይ፣ ሳይንከራተቱ የሚፈልጉትን አቅጣጫ ይዘው መጓዝ የሚችሉት እንዴት ነው?

 እበት ለቃሚ ጥንዚዛዎች በፀሐይ ወይም በጨረቃ ብርሃን እየተመሩ እንደሚጓዙ ቀደም ሲል የተደረጉ ጥናቶች አመልክተው ነበር፤ ይሁን እንጂ በጠፍ ጨረቃም ቀጥ ባለ መስመር መጓዝ ይችላሉ። የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች እንደገለጹት ጥንዚዛዎቹ ቀጥ ባለ መስመር የሚጓዙት ከዋክብትን በተናጠል በመመልከት ሳይሆን ፍኖተ ሐሊብ የተባለው ጋላክሲ የሚፈጥረውን ብርሃን በመከተል ነው። ከረንት ባዮሎጂ የተባለው መጽሔት እንደገለጸው “እንስሳት አቅጣጫ ለማወቅ የፍኖተ ሐሊብን ብርሃን እንደሚጠቀሙ በመረጃ የተደገፈ ማስረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።”

ማርከስ በርን የተባለ ተመራማሪ እንደገለጸው እበት ለቃሚ ጥንዚዛዎች “በእይታ አቅጣጫን የማወቅ ችሎታቸው ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በቂ የከዋክብት ብርሃን በሌለበት ጊዜም እንኳ ውስን በሆነው የአእምሮ ችሎታቸው ተጠቅመው አቅጣጫቸውን ጠብቀው መጓዝ ይችላሉ።” አክሎም እንዲህ ብሏል፦ “በእይታ አማካኝነት ሥራቸውን የሚያከናውኑ መሣሪያዎችን በመፈልሰፍ ረገድ የሚፈጠሩትን ውስብስብ ችግሮች መፍታት ስለሚቻልበት መንገድ የሰው ልጆች ከእነዚህ ነፍሳት ብዙ መማር ይችላሉ።” ለምሳሌ እበት ለቃሚ ጥንዚዛዎች አቅጣጫን የሚያገኙበትን ዘዴ በመኮረጅ በፈረሰ ሕንፃ ውስጥ ፍለጋ የሚያካሂዱ በርቀት መቆጣጠሪያ የሚሠሩ በራሪ ሮቦቶችን መሥራት ይቻላል።

  • ጄደብሊው ዶት ዖርግ (2014)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...