ግብዓት
- አራት ጭልፋ ውሃ
- አንድ ጭልፋ ምጥን ሽሮ
- አንድ ጭልፋ ዘይት ወይም ቅቤ
- ግማሽ ጭልፋ የተከተፈ ቲማቲም
- ጨው እንዳስፈላጊነቱ
አሠራር
- ቲማቲሙን በዘይት ወይም በቅቤ ማቁላላት
- ሲቁላላ ውኃ መጨመር
- ሲፈላ ሽሮውን ጨምሮ በደምብ ማብሰል
- ጨው እንደ ፍላጎት መጥኖ ማጣፈጥ
- ወጡ ሲበስል ማውጣት(በዘይት ከተሠራ ቀዝቃዛውን ማቅረብ ይመረጣል። በቅቤ ከተሠራ ግን ትኩሱን፡፡
- @እቴነሽ፤ ‹‹ባህላዊ ምግቦችና አሠራራቸው›› (2009)