ጭልፊቶች በኢትዮጵያ አብዛኛው አካባቢ ይታያሉ፡፡ እርድ በሚፈፀምባቸው ቦታዎች፣ ዓሣ በሚሠገርባቸው ሐይቆችና ሜዳማ ቦታዎች አይጠፉም፡፡ በየጎዳናው የተጣሉ ጥንቦችን ለማንሳትም የሚቀድማቸው የለም፡፡ ዶሮና ሥጋ ዓሣንም በመንጠቅ የምትታወቀው ጭልፊት በብሂል ውስጥ ትታወቃለች፡፡ ‹‹አጅሬ ጭልፊት ነውኮ›› እንዲል ምሰላው፡፡ ክረምት በሚበረታበት በሐምሌና በነሐሴ ወራት ከዕይታ ትርቃለች፡፡ የዶ/ር ከበደ ታደሰ የኢትዮጵያ መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ወፎች የኪስ መጽሐፍ ሁለገብ ጭልፊትን (Black Kite) ሙሉ አካሉ ጥቁር ቡናማ ቀለም ያለው አዳኝ ወፍ ነው በማለት ይገልጸዋል፡፡