Saturday, September 24, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር ለግዙፍ ፕሮጀክቶች ልዩ የመሬት ጨረታ አወጣ

  የአዲስ አበባ አስተዳደር ለግዙፍ ፕሮጀክቶች ልዩ የመሬት ጨረታ አወጣ

  ቀን:

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሪል ስቴትና ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴሎች ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች ለማስተላለፍ ልዩ ጨረታ አወጣ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣው ይህ ልዩ ጨረታ፣ ስምንት ቦታዎችን ብቻ የያዘ ቢሆንም ቦታዎቹ ሰፋፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

  ስድስቱ ቦታዎች ለሪል ስቴት ልማት፣ ሁለቱ ቦታዎች ደግሞ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ የሚውሉ ናቸው፡፡ ቦታዎቹ በአራት ክፍላተ ከተሞች የሚገኙ ሲሆን፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አራት ቦታዎች ለሪል ስቴት ልማት ቀርበዋል፡፡ ዝቅተኛው የቦታ ስፋት 14,089 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ ከፍተኛው ደግሞ 55,386 ካሬ ሜትር ነው፡፡ የቦታዎቹ መነሻ ዋጋ በካሬ ሜትር 191 ብር ሆኖ 60 ዓመት የሊዝ ዘመን ተሰጥቷቸዋል፡፡

  በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሁለት ቦታዎች ለጨረታ የቀረቡ ሲሆን፣ 23,913 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንድ የሪል ስቴት ቦታና 8,998 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው አንድ ቦታ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ ቀርቧል፡፡ የእነዚህ ቦታዎች የመነሻ ዋጋም በካሬ ሜትር 191 ብር ነው፡፡

  በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማም አንድ ቦታ ለሪል ስቴት ልማት ቀርቧል፡፡ የቦታው ስፋት 57,752 ካሬ ሜትር መነሻ ዋጋው በካሬ ሜትር 299 ብር ነው፡፡ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ውስጥ አንድ ቦታ ለባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ግንባታ የሚውል 6,014 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡

  ጨረታው እስከ ሐምሌ 23 ቀን ድረስ ይፋ ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በዚያው ዕለት ከሰዓት በኋላ ይከፈታል ተብሏል፡፡

  የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ፣ መሬት በዋነኛነት ለአልሚዎች የሚቀርበው በጨረታ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለቀላል ፕሮጀክቶች 14 ጊዜ ጨረታ አውጥቷል፡፡ ለሆቴል፣ ለሪል ስቴት፣ ለትምህርትና ለጤና ተቋማት ግንባታ የሚውሉ ቦታዎችን ለአልሚዎች ያቀረበው በሁለት ጨረታዎች ብቻ ነው፡፡

  የመጀመርያው ጨረታ ግንቦት 2 ቀን 2006 ዓ.ም. ወጥቶ ሰኔ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. መከፈቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ ጨረታም የወጡት ቦታዎች ሰፋፊ ቢሆኑም ቁጥራቸው አሥር ብቻ ነበር፡፡

  ባለሙያዎች አስተዳደሩ የመሬት ዋጋ ንረትን ለማርገብ በርካታ ቦታዎችን ለጨረታ ማቅረብ እንዳለበት ያሳስባሉ፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የአዲስ አበባን ንግድና ዘርፍ ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት በተደረገው ምርጫ አሸነፉ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በፕሬዚደንትነት ለመምራት፣...

  ለቻይናው ፖሊጂሲኤል ኩባንያ የተሰጠው ውል ተቋረጠ

  የማዕድንና ሚኒስቴር በሶማሌ ክልል የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት...

  የሕግ ክልከላዎችና የሚያስነሱት ቅሬታ

  በኢትዮጵያ የአገርና የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ተብለው የሚወጡ አንዳንድ ሕጎች፣...