Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልውበቷን በቅሪቷ ያስመሰከረችው ‹‹ስሊፒንግ ቢውቲ››

  ውበቷን በቅሪቷ ያስመሰከረችው ‹‹ስሊፒንግ ቢውቲ››

  ቀን:

  2,000 ዓመታትን ያስቆጠሩ የሮማን ኢምፓየርና የአክሱም ዘመነ መንግሥት ቅርሶች በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ ተገኝተዋል፡፡ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በእንግሊዛዊት አርኪዎሎጂስት የተገኙት ቅርሶች በአንደኛውና ሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

  አርኪዎሎጂስቷ ልዊስ ስኮፊልድ በጥንታዊቷ አክሱም ስድስት ሳምንት የወሰደ አሰሳ አድርገዋል፡፡ የሙያ አጋሮቻቸው ቅርሶቹ የተገኙባቸውን 11 መካነ መቃብሮች ለማግኘት ችለዋል፡፡ ቅርሶቹ ሮማውያን በአካባቢው ንግድ ያካሂዱ የነበረበት ወቅት ከዚህ በፊት በባለሙያዎች ከሚታሰበው 100 ዓመታት ወደ ኋላ የቀደመ መሆኑን አስረጂ ናቸው፡፡

  ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው ተመራማሪዋ በግኝታቸው ተገርመዋል፡፡ ‹‹በየቀኑ በርካታ ቅርሶች ከመሬት እያወጣን ነበር፤ ዓይኔን ማመን ነው የተሳነኝ፡፡ የሆነ ነገር እንደምናገኝ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ቢሆንም ይኼን ያህል ይሆናል ብዬ ስላልጠበቅኩ በጣም ተደስቻለሁ፤›› ብለዋል፡፡

  አርኪዎሎጂስቷን በጣም ያስገረማቸው ‹‹ስሊፒንግ ቢውቲ›› የሚል ስያሜ የሰጧት ሴት መካነ መቃብር ነው፡፡ የተቀበረችበት መንገድና በመቃብሯ የተገኙት ቁሶች እጅግ ውብና የተወደደች ሴት እንደነበረች ያመላክታል ብለዋል፡፡

  ሴቲቷ የተቀበረችው በአንድ ጎኗ አዘንብላ ፊቷን በአንድ እጇ አስደግፋ ነው፡፡ የነሐስ ቀለበት አድርጋለች፡፡ የሮማን ነሐስ መስታወት ከፊት ለፊቷ ተደርጎላታል፡፡ የኮስሞቲክስ ዕቃዎቿም እጅግ የተዋቡ ናቸው፡፡ አንገቷ ላይ ያለው ሀብልና ቀለበቷም ውድ ቁሶች ናቸው፡፡ አጠገቧ ጆግ፣ የአበባ ማስቀመጫና ሌሎችም ቁሳቁሶች ተገኝተዋል፡፡ ተመራማሪዋ ከሞት በኋላ ለሚኖረው ሕይወት ምግብና መጠጥ የተቀመጠባቸው እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ከፍተኛ ቦታ የነበራት ሴት እንደነበረችም ያመላክታል፡፡

  በ‹‹ስሊፒንግ ቢዊቲ›› መካነ መቃብር አቅራቢያ 1065 ባለ ደማቅ ቀለም ፈርጦች ያሉት ሀብል አድርጋ የተቀበረች ሴት አፅምም ተገኝቷል፡፡ አብሯት የሽቶ ጠርሙስ መገኘቱም ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

  ግኝቶቹ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ከሮም ጋር በቅርበት ይደረግ የነበረው ንግድ ውጤት እንደሚሆኑ የተናገሩት ተማራማሪዋ፣ ‹‹ኢትዮጵያ ምስጢራዊ አገር ናት፣ በርካቶች ግን ብዙ መረጃ የላቸውም፤›› ብለዋል፡፡

  ግኝቶቹ በቅርብ ወደሚከፈተው የጀርመን ሙዚየም ይወሰዳሉ፡ ተማራማሪዋ እ.ኤ.አ. በ2012 በተመሳሳይ አካባቢ የጥንት የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ቦታ ማግኘታቸውም ተዘግቧል፡፡ ግኝቱ የንግሥተ ሳባ ሀብት ከየት እንደመነጨ ፍንጭ ሰጪ መሆኑ ተገልጿል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...