የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ለስድስት ወራት የሚቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ዝርዝር መመሪያ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል አሉ፡፡
አዋጁ የወጣው በአገሪቱ እየታዩ ያሉ የፀጥታ ችግሮችንና የሰው ሕይወት መጥፋትን በመደበኛው የፀጥታ ማስከበር ሥራ ማስቆም ስላልተቻለ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ አዋጁን የሚያስፈጽም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮማንድ ፖስት እንደተቋቋመ ገልጸው፣ የፌዴራል ፖሊስን ጨምሮ የተለያዩ የፀጥታ አካላት በአባልነት የታቀፉበት እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡