ጥሬ ዕቃዎች
- ግማሽ ኪሎ ግራም የተቀቀለ የአበሻ ጐመን
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ደቆ በትንንሹ የተቆረጠ ድንች
- 2 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
- ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
- ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
- 1 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 3 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
አዘገጃጀት
1. ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ ማብሰል፤
2. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ማቁላላት፤
3. አዋዜ ጨምሮ ሙቅ ውኃ ጠብ እያደረጉ ማሸት፤
4. ቅቤና ርጥብ ቅመም መጨመርና ሽንኩርቱን በደንብ ማብሰል፤
5. ድንች ጨምሮ ውኃ ሳያበዙ ማብሰል፤
6. ጐመኑን አድቅቆ ከትፎ ከጥቁር ቅመም ጋር መጨመር፤
7. ድንቹ እንዳይፈርስ እየተጠነቀቁ በዝግታ ለጥቂት ጊዜ ማማሰል፤
8. መከለሻና ጨው አስተካክሎ ማውጣትና በትኩሱ ለገበታ ማቅረብ፡፡
– ደብረ ወርቅ አባተ ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2002)