‹‹ልጅ ታሞበት ማሳከም ያለበት የመንግሥት ሠራተኛ አይሳሳትም አትበሉ፡፡ ለልጁ ቤት ሲገባ ዳቦ ይዞ መግባት ያለበት አባት ልጁ በረሃብ እንዲሞት ይፈቅዳል ብላችሁ አታስቡ፡፡ ከእኛ ንግግር በላይ የሚያሸንፈው ነገር አለ፡፡››
ከሁለት ሳምንት በፊት የአስር ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርታቸውን ለፓርላማ ያቀረቡት የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን ኮሚሽኑ የሚሰጠው የሥነ ምግባር ትምህርት ምን ውጤት አስገኘ? የሚል ጥያቄ ከምክር ቤቱ አባላት ሲቀርብላቸው የሰጡት ምላሽ፡፡