Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ልናገርግንቦት 20 ለአካል ጉዳተኞች ምንም አላስገኝም?

ግንቦት 20 ለአካል ጉዳተኞች ምንም አላስገኝም?

ቀን:

በታዛቢ አካል ጉዳተኛ

ሰኔ 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በልናገር ዓምድ ላይ የቀረበውን ‹‹ግንቦት 20 ለአካል ጉዳተኞች ምን አስገኘ?›› የሚለውን ጽሑፍ ሳነብ በጣም የሚያሳዝን፣ ከጸሐፊውም የማይጠበቅ በመሆኑ እኔም በአካል ጉዳተኝነቴ እውነት መናገር አለብኝ፡፡ ሌሎቹም እንዲያወቁትና ጸሐፊው ያቀረበው ምንም ለውጥ እንደሌለ አካል ጉዳተኞችና ግንቦት 20 ሆድና ጀርባ ናቸው ማለቱ በጣም አሳፋሪ ዓይን ያወጣ ውሸት መሆኑ ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡ ጸሐፊው አሁን በጋዜጣው ላይ ሐሳቡን በነፃነት እንዲገልጽ ያስቻለውን የግንቦት 20 ውጤት እንዴት ሳይረዳ ይቀራል፡፡

መንግሥት ለአካል ጉዳተኞች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት፣ ክብርና ደኅንነት ለማስጠበቅ ተሳትፏቸውንና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም መካከል ሕጎችን ማውጣት፣ የልማትና የለውጥ ፖሊሲዎችን በመንደፍና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ብዙ ተግባራት አከናውኗል፡፡

ይህ እንዲህ እንዳለ የተደራሽነት መብታችንን ለማረጋገጥ መንገዶች፣ ሕንፃዎችና የሕዝብ መገልገያዎችን ምቹ ለማደረግ የሕንፃ አዋጅ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት አዋጅ መብት ከማስጠበቅም አንፃር አስፈላጊ የሆኑ መብቶችንም በአዋጅ በመደንገግ አመቺ ሁኔታዎች የመፍጠር ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ዕድል እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን፣ በጥቃቅንና በአነስተኛ ዘርፎች በማሳተፍ የመሥሪያ ቦታዎች፣ የሙያ ሥልጠናዎችን እንዲሁም የመሥሪያ መንቅሳቀሻ ካፒታል በማመቻቸት አካል ጉዳተኞች ከጠባቂነት ተላቀው ሕይወታቸውን በአግባቡ እየመሩ የሚገኙ በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህ በማኅበር ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አካል ጉዳተኞች በጀሞ፣ በፈረንሳይ፣ በሳሪስ፣ በዓለም ገና አከባቢ ያሉት ማየት ይቻላል፡፡

ሌላው የኮንደሚኒየም ቤቶችን በተመለከተ ለተጠቃሚዎች ሲተላለፉ ለሴቶች 30 በመቶ፣ ለመንግሥት ሠራተኞች 20 በመቶ፣ ለአካል ጉዳተኞች ለምን የሚል ነው፡፡ እዚህ ላይ ጸሐፊው እንዲገነዘብ የምፈልገው ሴት አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ አይደሉምን? አካል ጉዳተኛ ሆኖ በመንግሥት መሥሪያ ቤት የተቀጠሩ የሉም? እኛ አካል ጉዳተኞች ማለት ያለብን ከአካል ጉዳት ጋር በተያያዘ ያሉት ችግሮች በመጠኑም ቢሆን እየቀነሱ መጥተዋል፡፡ ከትናንትም ዛሬ የተሻለ ነው፡፡ ነገም ከዛሬው የተሻለ እንደሚሆን ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡ ምክንያቱም መንግሥት የሚያወጣቸው አዋጆችም ሆኑ ፖሊሲዎች አካል ጉዳተኞችን እያካተቱ ነው፡፡ ይህ የግንቦት 20 ወጤት ነው፡፡

ወደ ትምህርት ስንመጣ በ1986 ዓ.ም. የትምህርት ሥልጠና ፖሊሲ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጥ ማንኛውም ትምህርት በፍላጎታቸውና በአቅማቸው መሠረት መሆን እንዳለበት ይገልጻል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ አካል ጉዳተኞች በቁጥር ስናየው በእውነት መንግሥት ምን ያህል ትኩረት እንደሰጠ ለማንም የሚደበቅ አይደለም፡፡ የምልክት ቋንቋ አስተርጓሚ በዩኒቨርሲቲና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች መድቧል፡፡ ይኼንን ጸሐፊው እንዴት ያየዋል? ይህም የግንቦት 20 ውጤት ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲ ያለውን ሕንፃ ስንመለከት ጸሐፊው ማለት ያለበት የዩኒቨርሲቲው ሕንፃ የተሠራው የሕንፃ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት ወይስ በኋላ? ይህንን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ ጀምሮ የሚሠሩ ሕንፃዎች መመልከት ይቻላል፣ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ባቡሩም ሳይቀር ለአካል ጉዳተኞች ታሳቢ የተደረገ ነው፡፡ ይህም የግንቦት 20 ውጤት ነው፡፡ ጸሐፊው ማለት ያለበት ለውጡ እንዳለ ሆኖ የሚቀር ነገር አለና በቀጣይ ይስተካከሉልን ነው፡፡

በእኔ በኩል በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚፈጸመው አድልኦ እየቀነሰ ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ ተቀርፏል ማለት አይቻልም፡፡ ይህንንም ደረጃ በደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት መሞከር ነው፡፡ በተለይ በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ያሉት ማኅበራት መንግሥት ያወጣቸውን አዋጆችና ፖሊሲዎች ሙሉ ለሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ከባድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ችግሩን ቀስ በቀስ ለመፍታት መሞከር አለባቸው እላለሁ፡፡ ጸሐፊው አካል ጉዳተኞችና ግንቦት 20 ሆድና ጀርባ ናቸው የሚለው አባባሉ ተቀባይነት የለውም ባይ ነኝ፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...