Friday, April 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ቱርክ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የልማት ፋይናንስ ጉባዔ እንደምትሳተፍ አስታወቀች

ተዛማጅ ፅሁፎች

–  የቡድን ሃያ አገሮች በአፍሪካ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መስኮች ይፋ አደረገች

በብርሃኑ ፈቃደ ከቱርክ፣ ቦድሩም ከተማ

በመጪው ጥቅምት ወር ለሚካሄደው የቡድን ሃያ አገሮች የመሪዎች ስብሰባ፣ ከወዲሁ ዝግጅት የጀመረችውና የወቅቱ የቡድን ሃያ አገሮች ፕሬዚዳንቷ ቱርክ፣ ትኩረት ከምትሰጣቸው መካከል ከአንድ ወር በኋላ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የልማት ፋይናንስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍና የቡድን ሃያ አገሮችን የትኩረት አቅጣጫ ለማስተዋወቅ ዝግጅት ማድረጓ ተገለጸ፡፡

የቡድን ሃያ አገሮች የ      ቅድመ ጉባዔ ዝግጅት አስተባባሪ አምባሳደር ኤይስ ሲኒርሎው፣ ከዋና ከተማዋ ኢስታምቡል፣ 392 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው የሪዞርት ከተማዋ ቦድሩም ተገኝተው ለጋዜጠኞች እንዳብራሩት፣ አገራቸው የወቅቱን የቡድን ሃያ አገሮችን የወቅቱ ፕሬዚዳንትነት ከተረከበችበት ካለፈው ዓመት ማብቂያ ጀምሮ፣ በአሳታፊነት፣ በአፈጻጸምና በኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ቅድሚያ በመስጠት ትሠራለች፡፡ በተለይም በአፈጻጸም ላይ ትኩረት እንዲደረግ በማለት የወቅቱ ፕሬዚዳንትነቷን ተጠቅሟAnchor  የቡድን ሃያ አገሮችን እንደምትወተውት ይፋ አድርጋለች፡፡

አምባሳደሯ በአፍሪካ ትኩረት ስለሚደረግባቸው አዳዲስ የቡድን ሃያ አገሮች ዕቅዶች ሲገልጹም በኃይል መስክ፣ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና በልማት ሥራዎች ላይ የግል ባለሀብቶች በአፍሪካ ተሳትፎ ለመገፋፋት አገራቸው እንደምትሠራ ገልጸዋል፡፡ ከሰሐራ በታች ባሉ አገሮች ውስጥ ከሚገኙ 900 ሚሊዮን ሕዝቦች ውስጥ 600 ሚሊዮኑ ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኙ በመሆናቸው የቡድን ሃያ አገሮች ለኃይል ዘርፍ ትኩረት በመስጠት እንዲሠሩ ቱርክ ጥረት ታደርጋለች ተብሏል፡፡ ለዚህ አተገባበር የሚረዳ መራሔ ድርጊት እየተዘጋጀ እንደሚገኝም አምባሳደር ኤይስ ገልጸዋል፡፡ በመላው ዓለም 1.3 ቢሊዮን ሕዝቦች የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማያገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአፍሪካም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች ውስጥ በሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ወዳላቸው ታዳጊ አገሮች የሚላከው የሐዋላ ገቢና የሚያስወጣው ወጪን ለመቀነስ የሚያስችል ሥራ ካላፈው ዓመት ጀምሮ ቱርክ እየሠራች መሆኗን የገለጹት አምባሳደሯ፣ ገንዘብ በሐዋላ ለመላክ የሚጠይቀውን ከ12 እስከ 15 ከመቶ የመላኪያ ወጪ ወደ አምስት ከመቶ የማውረድ ዕቅድ አገራቸው ይዛ እየተገበረች መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሐዋላ ገንዘብ በአፍሪካ የሚገኙትን ጨምሮ ወደተለያዩ አገሮች መላኩ ይታወቃል፡፡

የአፍሪካና የሌሎች አካባቢ የፋይናንስ ሚኒስትሮች የተሳተፉበትና የሚገጥሟቸው ችግሮች ላይ ውይይት የተደረገበት መድረክ በቱርክ አማካይነት ለመጀመሪያ ጊዜ በቡድን ሃያ አገሮች ክበብ ውስጥ መካሄዱ ተገልጿል፡፡ ‹‹ቲንክ 20፣ ሲቪል 20፣ ዩዝ 20፣ ቢዝነስ 20›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸውን ጨምሮ በሌሎችም ቡድኖች የተዋቀሩ አካላትና ባለሙያዎች ተሰባስበው በመወያየት የመፍትሔ ሐሳቦችን ለመሪዎች፣ በአዘጋጆች በኩል የሚያቀርቡበት አሠራር የተዘረጋ ሲሆን፣ ‹‹ቲንክ 20›› ወይም የባለሙያዎች ቡድን ትልቁና ከዓለም ትልልቅ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚያድርጉበት ቡድን ነው፡፡

በዚህ ቡድን ውስጥ ተሳትፎ ሲያደርጉ ከነበሩት መካከል ዶ/ር ራሔል ካሳሁን አንዷ ናቸው፡፡ ዶ/ር ራሔል ‹‹አፍሪካ አንባውንድ›› የተባለ ተቋም በግላቸው መሥርተው በዋና ዳይሬተርነት የሚያስተዳድሩ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ በአፍሪካ ኅብረት፣ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ እንዲሁም በአፍሪካ ልማት ባንክ ጥምረት የተመሠረተውን ‹‹ኮኣሊሽን ፎር ዳያሎግ ኦን አፍሪካ›› የተሰኘ ተቋም በዋና አስፈጻሚነት እየመሩ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር ራሔል በቱርክ ቆይታቸው ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ በቡድን ሃያ አገሮች መካከል ያለው የባለሙያዎች የምክክር ቡድን ወይም ቲንክ 20 ለመሪዎች ከሚያቀርባቸው የመፍትሔ ሐሳቦች ውስጥ የዓለምን የፋይናንስ ሥርዓት የሚያንቀሳቅሱት እንደ የዓለም የገንዘብ ድርጅት እንዲሁም የዓለም ባንክ ተከልሰው በድጋሚ እንዲዋቀሩ መደረግ አለበት የሚለው ይገኝበታል፡፡ በተለይ እ.ኤ.አ. በ2008/09 የተከሰተው የዓለም የፋይናንስና ኢኮኖሚ ቀውስ እስካሁን እያደረሰ ላለው ተፅዕኖ ተወቃሽ የሚደረጉት እነዚህ ተቋማት፣ መሻሻል ብቻ ሳይሆን ጠበቅ ያለ ቁጥጥርና ክትትል ሊደረግባቸው እንደሚገባ ምሁራኑ እየመከሩ ይገኛል፡፡

እነዚህ ተቋማት ከአስተዳደር ችግሮች ጀምሮ በርካታ ጉድለቶች እየታዩባቸው በመምጣቱ ማሻሻያ ሊደረግባቸው እንደሚገባ ጥያቄ እየቀረበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር የእስያ አገሮች ያቋቋሙት የኢንቨስትመንትና የመሠረተ ልማት ባንክ፣ እንዲሁም ብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ (ብሪክስ) የመሠረቱት ‹‹ብሪክስ ባንክ›› ዋሽንግተን ላይ የከተሙትን ኃያል ተቋማት ከመቋቋም አልፎ ለአፍሪካ አገሮች ትልቅ ዕድል መሆኑን ዶ/ር ራሔል ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ራሔል እንዳብራሩት፣ በርካታ ድሃ አገሮች ብድር ለማግኘት አማራጭ ገበያ የሚሆኑ ተቋማት ስለመጡላቸው በአነስተኛ ወለድና የክፍያ ጫና ገንዘብ ማግኘት የሚችሉበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡

በቡድን ሃያ አገሮች መካከል በንግድ፣ በሥራ ዕድሎች ፈጠራ፣ በመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በፋይናንስ ተቋማት ሪፎርም፣ በልማት መስኮች ላይ ትኩረት የሚደረግበት የዘንድሮው የቡድን ሃያ አገሮች ጉባዔ በመጪው ኅዳር ወር የሚካሄድ ሲሆን፣ ይህንን ጉባዔ በማስመልከት፣ የቡድን ሃያ አገሮች የወቅቱ ፕሬዚዳንት እንደመሆኗ ቱርክ፣ ልዑካኖቿን ወደ አዲስ አበባ በመላክ የልማት ፋይናንስ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ማቀዷም ተሰምቷል፡፡

የቡድን ሃያ አገሮች ስብስብ የተፈጠረው እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ ውስጥ በእስያና በሩስያ አገሮች የተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ያስከተለውን ውጥንቅጥ ተከትሎ ነው፡፡ ቡድን ሃያ እንዲመሠረት ሐሳብ ያቀረቡት በወቅቱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ፖል ብሬተን ናቸው፡፡ በዓለም ግዙፍ ኢኮኖሚ ያላቸውና በጋራ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ሃያ አገሮች የመሠረቱት ይህ ቡድን፣ በርካታ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ቢታመንበትም የታሰበውን ያህል የዓለምን ራስ ምታት ማስታገስ ሳይቻለው ቆይቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች