Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትየወፎች ውስጣዊ የአካል እንቅስቃሴ

  የወፎች ውስጣዊ የአካል እንቅስቃሴ

  ቀን:

  የወፎች ውስጣዊ የአካል እንቅስቃሴ የሚያያዘው በአብዛኛው በመጠን አነስተኛና በራሪ እንስሳት ከመሆናቸው አንፃር ነው፡፡ አነስተኛና በራሪ መሆናቸው አካላቸውን ከፍተኛ ኃይል እንዲጠቀም ያስገድደዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የውስጣዊ አካላቸው እንቅስቃሴ የተወሰነው ይህንን ከፍተኛ የአካል ሙቀት (ኃይል) በማምረት ላይ ነው፡፡

  አመጋገባቸው

  ወፎች ፍራፍሬ፣ ሦስት አፅቅ፣ ጥራጥሬ፣ ሥጋና የአበባ ወለላን በዋነኛነት በመመገብ ይታወቃሉ፡፡ ከዚህ ውጪ በአመጋገብ ምርጫቸው ምክንያት መርጠው የሚበሉና የተገኘውን የሚበሉ በመባል ይለያሉ፡፡

  መርጠው የሚመገቡ

  እነዚህ ወፎች ውስን የአበላል ሥርዓት ያላቸውን የተወሰነ ምግብ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ ናቸው፡፡ እኒህ ዓይነቶቹ በአካባቢያቸው ድርቅ በመጣ ወቅት ተጎጂዎች ይሆናሉ፡፡ ለአደጋም የተጋለጡ ናቸው፡፡ ደግነቱ አብዛኞቹ አዕዋፍ ይህንን ዓይነቱን የአመጋገብ ስልት የሚከተሉ አይደሉም፡፡

  ያገኙትን የሚመገቡ

  እነኚህ ዓይነት ወፎች ሰፋ ያለ የምግብ ምርጫ ያላቸው ሲሆኑ፣ በአካባቢያቸው በየወቅቱ በብዛት ሊገኙ የሚችሉትን ምግቦች በሙሉ የሚመገቡ ናቸው፡፡ ይህ ለአዕዋፍ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች እንስሳትም ተመራጭ የአመጋገብ ሥርዓት ነው፡፡ ለአደጋም አያጋልጥም፡፡ ይህ ዓይነት አመጋገብ ሰውንም ለድርቅ አደጋ በቀላሉ እጁን ሰጥቶ ለረሃብ እንዳይጋለጥ ይረዳዋል፡፡ በመሆኑም አብዛኞቹ ወፎች የሚተገብሩት አመጋገብ ሆኖ ይገኛል፡፡

  ጉደኛ በላተኝነት

  በአጠቃላይ ስለወፎች አመጋገብ ስንገልጽ ምግባቸው መጠነ ብዙ መሆኑን መጥቀስ ያስፈልጋል፡፡ ይህም ከላይ እንደተጠቀሰው ከፍተኛ የሆነ የአካል ሙቀታቸውን ለመጠበቅና ቀልጣፋ እንቅስቃሴያቸውን ለመታደግ ብዙ ኃይል (ጉልበት) ስለሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ የዚህ ኃይል ምንጭ ደግሞ ምግብ በመሆኑ ነው፡፡ እናም አንድ ሰው እንደ ወፍ ነው የሚበላው ከተባለ ከፍተኛ የምግብ ፍላጎት አለው ማለት ነው፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን እዛው ወፎች ጋርም አነስተኛ ክብደት ያላቸው ወፎች ከፍ ካሉት ይልቅ የበለጠ የሚመገቡ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ወፎች ከፍ ካሉት አነስተኛ ክብደት ያላቸው ወፎች ከፍ ካሉት ይልቅ የበለጠ የሚመገቡ ናቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ጉዳይም በሁሉም እንስሳት ላይ የሚታይ ነው፡፡

  ሁልጊዜም አነስተኛ እንስሳት ከአካላቸው ክብደት አንፃር ሲታይ ከፍተኛ በላተኞች ናቸው፡፡ ምሳሌ ብንወስድ፣ አንድ ሕፃን ልጅ በቀን ውስጥ ከክብደቱ አንፃር ሲሰላ ከአዋቂ የበለጠ ይመገባል፡፡ አንዲት አይጥ ከክብደቷ አንፃር ሲለካ በቀን ውስጥ ከትልቁ ዝሆን የበለጠ ትመገባለች፡፡ የዚህም ዋና ምክንያት የአካላቸውን ሙቀት በተወሰነ ደረጃ ለመጠበቅ በሚያደርጉት ግብረ-አካላዊ እንቅስቃሴ ነው፡፡ አነስተኛ እንስሳት ከትልልቆቹ አንፃር ሲትይ የበዛ ኃይል በፍጥነት ስለሚያወጡ፤ በዛው መጠን ተገቢውን ኃይል በፍጥነት መተካት ይኖርቦቸዋል፡፡ ስለዚህም የበለጠ ይመገባሉ፡፡ ይህንን ዘርዘር ስናደርገው፤ አነስተኛ አይጦች በቀን የአካላቸውን ክብደት ያህል ይመገባሉ፡፡ ይህም ዝሆን የአይጦቹን ያህል በቀን ይመገባል ለማለት የክብደቱን ያህል መመገብ አለበት ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት በቀን ከአንድ ሺሕ ኪሎ ግራም እስከ ሁለት ሺሕ ኪሎ ግራም ይመገባል ማለት ነው፡፡ ይህ ግን የሚሆን አይደለም፡፡ እናም ሁሌም አነስተኛ እንስሳት እንቅስቃሴያቸው ከፍተኛ በመሆኑ ኃይልን አብዝተው ስለሚፈልጉ ከትልልቆቹ አንፃር የሚመገቡት የምግብ መጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የአካል ሙቀታቸውን በተወሰነ ደረጃ ለመጠበቅ ያወጡትን ኃይል ያህል መተካት ግድ ይላቸዋል ማለት ነው፡፡

  አዕዋፍ ደግሞ ከሌሎች እንስሳት አንፃር በአጠቃላይ ሲታዩ አነስ ያለ የአካል ክብደት ስላላቸውና እንቅስቃሴያቸው ፈጣንና መብረርን የሚጨምር በመሆኑ፤ የኃይል ምንጭ የሆነውን ምግብ አብዝተው ይወስዳሉ፡፡ የተመገቡት ምግብም ለአካላቸው እንቅስቃሴ ይረዳ ዘንድ በፍጥነት መቃጠልና ወደኃይልነት መለወጥ ይኖርበታል፡፡ ለዚህም የአተነፋፈስ ሥርዓታቸው በጣም የተቀላጠፈና ፍቱን መሆኑ ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡

  • ማንይንገረው ሽንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)
  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...