Tuesday, December 10, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ግርታ›› በዘጠነኛው ሪቨር ፊልም ፌስቲቫል አሸነፈ

‹‹ግርታ›› በዘጠነኛው ሪቨር ፊልም ፌስቲቫል አሸነፈ

ቀን:

spot_img

በዘጠነኛው ሪቨር ፊልም ፌስቲቫል ላይ በአጫጭር ፊልሞች ዘርፍ ‹‹ግርታ›› የተሰኘ የኢትዮጵያ ፊልም ማሸነፉ ታውቋል፡፡ በማንተጋፍቶት ስለሺ የተሠራው ‹‹ግርታ›› ፊልም በታሪክ አወቃቀር፣ በዝግጅት፣ በአርትኦት እንዲሁም በታሪክ ፍሰቱ የላቀ በመሆኑ እንደተመረጠ የፌስቲቫሉ ድረ ገጽ የፌስቲቫሉን ዳኞች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ የፊልሙ ተዋንያን ብቃትም ከግምት ውስጥ እንደገባ ተገልጿል፡፡

ማንተጋፍቶት በፌስቡክ ገጹ በማሸነፉ የተሰማውን ደስታ ገልጿል፡፡ ‹‹በመጀመሪያ አጭር ፊልሜ ያገኘሁትን ሽልማት ጣልያን፣ ፓዶቫ ተገኝቼ ተቀብያለሁ፤›› ሲል ገልጿል፡፡ ከፊልሙ ባለሙያዎች መካከል ሲኒማ ቶግሪፈርና ኤዲተር ዳንኤል ታምራት፣ እንዲሁም ረዳት ዳይሬክተር ዘላለም ጌታሁን ይገኙበታል፡፡

ማንተጋፍቶት ለሦስት ዓመታት በዘጋቢ ፊልም አዘጋጅነት በማስታወቂያ ድርጅት ውስጥ ሠርቷል፡፡ አቡጊዳ ፕሮ አድቨርታይዚንግ የተሰኘ ድርጅት ከፍቶ 12 ዘጋቢ ፊልሞችና ከ300 በላይ የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ሠርቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2007 ወደ ጀርመን ያቀናው ማንተጋፍቶት፣ እዚያው በትምህርትና ሥራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከጀርመናዊ የፊልም አዘጋጅ ጋር ተጣምሮ ‹‹100 ይርስ ኢትዮ-ጀርመን ዲፕሎማቲክ ሪሌሽን›› የተሰኘ ፊልም ሠርቷል፡፡

በውድድሩ ላይ ከ118 አገሮች የተውጣጡ 4,852 ፊልም ሠሪዎች እንዲሁም 16 ዩኒቨርሲቲዎችና የፊልም ትምህርት ቤቶችም ተሳትፈውበታል፡፡

ማንተጋፍቶት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቲያትር ጥበባት ትምህርት ቤት በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም ከጀርመን በጆርናሊዝም ኤንድ ኮሚዩኒኬሽንስ በሁለተኛ ዲግሪ ተመርቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከምክክርና ከድርድር ውጪ ምን ዓይነት አማራጭ ይኑረን?

በዘውዳለም መንገሻ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውዝግብ በትንሹ የአንድ ምዕተ ዓመት...

ነፃነትና ሰንሰለት

(ክፍል አንድ) በታደሰ ሻንቆ 1) ‹‹ውስጣዊ ሰንሰለቶች እንዳሉ ሁሉ ውጫዊ ሰንሰለቶችም...

ገበያውን ሊያረጋጉ የሚችሉ አዳዲስ መፍትሔዎችን ማምጣት ያስፈልጋል!

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎንፌ (ዶ/ር) በሕዝብ...

አዲሱ የሕንፃ አዋጅ ‹ድርጅት ተኮር› ሳይሆን ‹ባለሙያ ተኮር› ተደርጎ መዘጋጀት አለበት የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር

የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማኅበር በቀድሞ የሕንፃ አዋጅ የነበረውን ‹‹ባለሙያ ተኮር››...