Wednesday, October 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የ120 ሚሊዮን ዶላር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ስምምነት ተፈረመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኢትዮጵያና ኬንያን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማገናኘት፣ በኢትዮጵያ በኩል የ433 ኪሎ ሜትር ኃይል ማስተላለፊያ መስመር መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱ ሰኔ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀና ግንባታውን ለማካሄድ የተመረጠው የቻይናው ስቴት ግሪድ እህት ኩባንያ ሲኢቲ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ቸንግ ዊ በሸራተን አዲስ ተፈራርመዋል፡፡ የኃይል መስመሩ አንደኛው ኮንትራት በ120 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የሚገነባ ሲሆን፣ ወጪው በአፍሪካ ልማት ባንክ ይሸፈናል ተብሏል፡፡ ግንባታው ከወላይታ ሶዶ ተነስቶ ኬንያ ድንበር ሞያሌ ላይ የሚቆም ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን 612 ኪሎ ሜትር የኃይል መስመር ኬንያ ትገነባለች፡፡ ኢትዮጵያ 400 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬንያ ለመሸጥ ስምምነት ያረገች በመሆኗ፣ አንዱን ኪሎ ዋት በሰባት የአሜሪካ ሳንቲም ለመሸጥ ስምምነት ተደርጓል፡፡ የቻይናው ኩባንያ የፈረመው በኢትዮጵያ በኩል ከሚገነቡት ሁለት ኮንትራክተሮች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በቅርቡ አንደኛው ኮንትራት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በኬንያ በኩል የሚገነባው የኃይል መስመር በሦስት ኮንትራቶች የተከፈለ ነው፡፡ ግንባታውን ለማካሄድ አሸናፊ ከሆኑ የህንድ ኩባንያዎች ጋር በቅርቡ ስምምነት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ግንባታ በ26 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡ የቻይናው ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንትም ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ገደብ እንደሚጠናቀቅ ቃል ገብተዋል፡፡ በምሥሉ ላይ ኢንጂነር አዜብ አስናቀና የቻይናው ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ቸንግ ዊ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች