Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትእግር ኳስ ፌዴሬሽን ለተጨዋቾች ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበረከተ

እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለተጨዋቾች ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበረከተ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡ ሽለማቱ ተጨዋቾች በተጫወቱበት የሰዓት መጠን ተሰልቶ የተሰጠ መሆኑም ተናግሯል፡፡

ለ2017 የአፍሪካ ዋንጫና ለ2016 ቻን ከሌሴቶና ኬንያ ብሔራዊ ቡድኖች ጋር የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያውን አድርጎ በአሸናፊነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊት ለፊቱ ለሚጠብቀው ወሳኝ ግጥሚያዎች የሞራል ስንቅና ላስመዘገበው ውጤት እውቅና ለመስጠት እንጂ ሽልማቱ በቂና የሚያኩራራ ነው ተብሎ እንደማይወሰድ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጁነዲን ባሻ በሥነ ሥርዓቱ ተናግረዋል፡፡

ሰኔ 16 ቀን 2007  ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል በተከናወነው የሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት፣ ለብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ 25,000 ብር፣ ለምክትሉ ፋሲል ተካልኝ 15,000 ብር፣ ለበረኞች አሠልጣኝ አሊ ረዲ የ10,000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ለቡድኑ ዶ/ር አያሌው ጥላሁንና ለወጌሻ በኃይሉ አበራ የሽልማቱ መጠን ባይጠቀስም የገንዘብ ማበረታቻው ተበርክቶላቸዋል፡፡

ለተጨዋቾች ሙሉ 90 ደቂቃ ለተጫወቱ 20,000፣ ከ90 ደቂቃ በታች ለተጫወቱ ደግሞ 15,000፣ ከ45 ደቂቃ በታች ለተጫወቱ 10,000 እና ለተጠባባቂ ተጫዋቾች 7,000 ብር ተሰጥቷቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰኔ 28 ቀን በናይሮቢ ኬንያ ለሚደረገው የቻን የመልስ ጨዋታ ዋሊያዎቹ የክለቦች ጥሎ ማለፍ ጨዋታ የማይመለከታቸው ተጨዋቾች ሰኔ 17 ቀን ለዝግጅት ወደ ሐዋሳ ማምራታቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡ የክለቦች ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሐሙስ ሰኔ 18 እና ዓርብ ሰኔ 19 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀጥሎ እንደሚውልም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...