‹‹በአየር ንብረት መዛባት ሳቢያ ዓለማችን ትልቋ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ሆናለች፡፡››
የሮም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹ፖፕ›› ፍራንሲስ በቅርቡ ከቫቲካን አፈትልኮ ወጣ በተባለ ሰነድ ውስጥ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ፖፕ ፍራንሲስ ይህ ሰነድ አፈትልኮ ከወጣ በኋላ እሳቸው የሚመሯት ቫቲካን በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ያወጣችው ዳጎስ ያለ ሰነድ የዓለም መነጋገሪያ እየሆነ ሲሆን፣ በሰነዱም ላይ ሰጡት በተባለው ማብራሪያ ምክንያት በዓለም ዙሪያ ትኩረት ማግኘታቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ፖፕ ፍራንሲስ ለዓለም መሪዎች ባቀረቡት ምልጃ፣ ‹‹የዓለምንና የድሆችን ለቅሶ ማዳመጥ አለባችሁ፤›› ብለዋል፡፡ የፖፕ ፍራንሲስ ማሳሰቢያ ከተሰማ ወዲህ፣ በጉዳዩ ላይ መጣጥፎቻቸውን በታዋቂ ሚዲያዎች ላይ ያቀረቡ ጸሐፍት የበለፀጉ አገሮች መሪዎች የእሳቸውን ያህል ትኩረት የላቸውም ብለዋል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ናቸው፡፡