Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊትውልደ ኢትዮጵያዊው ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆነ

ቀን:

በእንግሊዝ ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ለቻንስለርነት ከተወዳደሩ ሦስት ግለሰቦች መካከል ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገጣሚና ጸሐፈ ተውኔት ለምን ሲሳይ አብላጫውን ድምፅ በማግኘት አሸነፈ፡፡ ለምን በወድድሩ የተሳተፉትን የሙዚቃ ባለሙያውን ሰር ማርክ ኤልደርና የቀድሞውን የእንግሊዝ ፖለቲከኛ ሎርድ ፒተር ማንዴልሰንን ሰፊ በሆነ የድምፅ ብልጫ አሸንፏል፡፡

ለምን ውድድሩን ያሸነፈው 7,131 የማንቸስተር ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞችና የቀድሞ ተማሪዎችን ድምፅ በማግኘት ሲሆን፣ ሰር ማርክ ኤልደር 5,483 ድምፅ በማስመዝገብ ሁለተኛ ሆነዋል፡፡ እንዲሁም ፖለቲከኛው ሎርድ ፒተር 5,269 ድምፅ በማግኘት ሦስተኛ ሆነዋል፡፡

ለምን ከምርጫው በኋላ የዩኒቨርሲቲው ቻንስለር ለመሆን ያበቃውን ድምፅ የሰጡትን መራጮች አመስግኗል፡፡ ከነሐሴ አንድ ጀምሮ በሥልጣን ላይ ያሉትን ቶም ብሎክሳምን ተክቶ ለሰባት ዓመታት እንደሚሠራ ታውቋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዴም ናንሲም ዩኒቨርሲቲውን በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

ገጣሚና ጸሐፊ ተውኔት ለምን ሲሳይ እ.ኤ.አ. በ1967 በዊጋን ከተማ ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የተወደለ ሲሆን፣ ከወላጆቹ ዘንድ ለማደግ አልታደለም ነበር፡፡ እስከ 12 ዓመቱም እንግሊዛዊ አሳዳጊዎቹ ዘንድ ቆይቷል፡፡ በኋላም በአካባቢው በሚገኝ ሕፃናት ማሳደጊያ ዕድሜው 17 እስኪሆን ቆይቷል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1988 በ21 ዓመቱ የግጥም መድበል አሳትሟል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1995 ‹ኢንተርናል ፍላይት› የሚባል በቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ ለዕይታ አብቅቷል፡፡ ሌሎች በርካታ ስኬቶችም ተቀዳጅቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...