Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተፈጸሙ በደሎችን በማረም ረገድ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዳስቸገረው...

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተፈጸሙ በደሎችን በማረም ረገድ አዲስ አበባ አስተዳደር እንዳስቸገረው ገለጸ

ቀን:

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በደረሱት የአስተዳደራዊ በደል ጥቆማዎች ላይ ተመሥርቶ በሚያደርገው ምርመራ የመፍትሔ ሐሳቦችን ቢያቀርብም፣ አንዳንድ መሥሪያ ቤቶች እምቢተኝነት እያሳዩ መሆናቸውን አስታወቀ፡፡ ከእነዚህም መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ገለጸ፡፡

ዋና የሕዝብ እንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ፎዚያ አሚን የተቋማቸውን የአሥር ወራት የሥራ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት፣ በአስተዳደር ጥፋት ምክንያት የደረሰ በደል እንዲታረም የተመርማሪ መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ትብብርና ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር በደል አቤቱታዎች ሲደርሱት አልያም በተደጋጋሚ ከሚደርሰው ጥቆማ በመነሳት የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ የገለጹት ወ/ሮ ፎዚያ፣ በምርመራው መሠረት የመፍትሔ ሐሳቦችን ለሚመለከታቸው ተቋማት እንደሚልክና የመፍትሔ ተቀባይነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

ሆኖም የተወሰኑ አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች በተቋሙ የምርመራ ውጤት ላይ ተንተርሶ በተላከላቸው የመፍትሔ ሐሳቦች መሠረት አለመፈጸም ወይም የማይፈጸሙበት በቂ ምክንያት ካላቸው ለተቋሙ ያለመግለጽና በምርመራ ሒደት አስፈላጊውን ትብብር ያለማሳየት እንቢተኝነት እንደሚታይ ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህም ተቋማት መካከል በተደጋጋሚ ስሙ የተገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው፡፡ ከአስተዳደሩ አካላት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና ክፍለ ከተሞች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም የኦሮሚያ የአርሲ ዞን አስተዳዳር ጽሕፈት ቤት፣ የምሥራቅ ሸዋ ዞን አስተዳዳር ጽሕፈት ቤት፣ የሐዋሳ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና በሐረሪ ክልል የፍትሕና የፀጥታ ጉዳይ ቢሮ በእነዚህ ችግሮች የተጠቁ መሆናቸውን ዋና እንባ ጠባቂዋ ወ/ሮ ፎዚያ ገልጸዋል፡፡

የተገለጹት ተቋማት በቀረበላቸው የመፍትሔ ሐሳቦች መሠረት የእርምት ዕርምጃ ባለመውሰዳቸው ልዩ ሪፖርት ለፓርላማው የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳዳር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዝርዝር መላካቸውን የጠቀሱት ወ/ሮ ፎዚያ፣  ቋሚ ኮሚቴው ባደረገው ክትትል በደሎቹ በከፊል የታረሙ መሆኑን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አለመቀረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ራሱ ተቋሙ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ለምን እነዚህን ተቋማት እንደማያስቀጣ የተጠየቁት ዋና እንባ ጠባቂዋ፣ በአስተዳደራዊ በደል አቤቱታ ላይ ምርመራን መሠረት ያደረገ የመፍትሔ ሐሳብ አቤቱታ ለቀረበበት ተቋም የሚቀርብ መሆኑን ገልጸው፣ ተቋሙ በቂ ምክንያት ካለው ይኼንኑ ገልጾ የመፍትሔ ሐሳቡን ላለመተግር እንደሚችል በአዋጁ መደንገጉን ተናግረዋል፡፡

‹‹በቂ ምክንያት ካለው›› የሚለው ሐረግ ለትርጉም ክፍት በመሆኑ ዕርምጃ ለመውሰድ እንዳላስቻላቸው የገለጹት ወ/ሮ ፎዚያ፣ ይኼን ችግር ለመቅረፍ አዋጁን ለማሻሻል በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...