አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 15 አውንስ የቲማቲም ስጎ
- ሦስት የሾርባ ማንኪያ ፕርሜዥያን ቺዝ
- ሁለት የሾርባ ማንኪያ የተከተፈ ቲማቲም
- አንድ የሾርባ ማንኪያ ደርቆ የተወቀጠ ጎመን/ስፒናች
- ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ቀይ ቃሪያ
- ሩብ ኪሎ ለጋ ስፒናች (ያልደረቀ)
- ሁለት የሾርባ ማንኪያ ዘይት
- ግማሽ ኪሎ ሊጥ (ለፒዛ በሚመች መልኩ ደረቅ ብሎ የተቦካ)
- ሁለት ኩባያ በስሱ የተቆራረጠ ሞዞሬላ ቺዝ
አዘገጃጀት
- መጋገሪያ ኦቨኑን በ475 ዲግሪ ፋራናይት ቀድሞ ማሞቅ፣
- የቲማቲም ስጎውን፣ ፕርሜዥያን ቺዙን፣ የተከተፈ ቲማቲሙን፣ ደርቆ የተዘጋጀውን ጎመን/ስፒናች፣ የተከተፈውን ቀይ ቃሪያ ባንድ ሳህን ማደባለቅ
- ደቆ የተከተፈውን ለጋ ስፒናች ከሁለት የሾርባ ማንኪያ ውኃ ጋር ማደባለቅና ማብሰል
- የተቦካውን ሊጥ በመጋገሪያ (ፓትራ) አድርጎ ኦቨን ውስጥ በመክተት ለሦስት ደቂቃ ያህል በመካከለኛ ሙቀት ማብሰል
- ከኦቨኑ አውጥቶ ተደባልቀው የተዘጋጁትን በላዩ ላይ መቀባት
- የበሰለውን ስፒናች በላዩ ላይ መነስነስ
- የተደበላለቁት ግብዓቶችና ቺዙ ቡናማ እስኪሆን ድረስ በኦቨን ውስጥ ከቶ ለ15 ደቂቃ ማብሰል (ቡናማ መልክ እስኪያመጣ)
- ከኦቨኑ አውጥቶ ለአምስት ደቂቃ ማስቀመጥና መመገብ