Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ሥነ ፍጥረትታዳኞቻቸውን የሚያታልሉ

  ታዳኞቻቸውን የሚያታልሉ

  ቀን:

  አንግለር (Angler) የተባሉ የዓሣ ዝርያዎች ታዳኞቻቸውን የሚስቡና የሚያታልሉበት የተለየ መንገድ አላቸው፡፡ ይኸውም ከአፋቸው በላይ በሚንሳፈፈው አንቴና በሚመስል የአካል ክፍላቸው አማካይነት ነው፡፡ አንግለሮች ከጭቃ (ውኃ ስር) በመደበቅ በሰፊው ከተከፈተው አፋቸው በላይ ማታለያ የሆነውን አንቴና መሰል የአካል ክፍል ያንቀሳቅሱታል፡፡ በዚህ እንቅስቃሴ ተስቦ ምን እንደሆነ ሊያረጋግጥ የመጣ ማንኛውም ታዳኝ ዕጣ ፈንታው በሰፊው በተከፈተ አፍ ውስጥ ገብቶ መዋጥ ይሆናል፡፡ አንግለሮች የሚታወቁት እነሱ ጋ ሊደርስ የሚችል ማንኛውንም ሕይወት ያለው ነገር በመመገብ ነው፡፡ አልፎ አልፎ የባሕር ላይ ወፎችንም ያድናሉ፤ ለምሳሌ ዳክዬ፡፡ በዚህም አንግለሮች ከእነሱ የበለጠ መጠን ያለውን ሕይወት ያለው ነገር በመዋጥ ይታወቃሉ፡፡ ሆዳምነታቸውን አንዳንዴ ጉጉ ያደርጋቸውና ከእነሱ በእጥፍ መጠን የሚበልጡ ዓሣዎችን በልተው የሚያደርጉት ጠፍቷቸውና ተጨንቀው ውኃ ላይ ሲንሳፈፉ ይስተዋላሉ፡፡ የጥርሳቸው አበቃቀል አንዴ ታዳኞቻቸውን ከያዙ እንዳይለቁ እንዲያደርግ ሆኖ ነው፡፡ ስለዚህም የያዙትን ምግብ በልተው ካልጨረሱ ከጥርሳቸው አያላቅቁም፡፡ ሌሎች ከአንግለሮች ያነሱ የባሕር ስር ዓሣዎችም እንደ አንግለሮች ወይም ከእነሱ በበለጠ ታዳኞቻቸውን የመዋጥ ችሎታ አላቸው፡፡ እነዚህ ዝርያዎች ሰፊ አፍ ሲኖራቸው፣ በመጠን ከእነሱ ሦስት እጥፍ የሚሆናቸውን ዓሣዎች መዋጥ ይችላሉ፡፡

  • ማንይንገረው ሽንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img