Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅበስልጤ ዞን የገባባ ጤና ኬላ ግቢ ውስጥ በአካባቢው ነዋሪዎች መዋጮ የተገነባና ማንኛዋም...

በስልጤ ዞን የገባባ ጤና ኬላ ግቢ ውስጥ በአካባቢው ነዋሪዎች መዋጮ የተገነባና ማንኛዋም ወላድ ከመውለጃዋ ቀን ቀደም ብላ በመምጣት የምታርፍበት ክፍል

ቀን:

በስልጤ ዞን የገባባ ጤና ኬላ ግቢ ውስጥ በአካባቢው ነዋሪዎች መዋጮ የተገነባና ማንኛዋም ወላድ ከመውለጃዋ ቀን ቀደም ብላ በመምጣት የምታርፍበት ክፍል ሲሆን፣ በውስጡ ቴሌቪዥንና ሬዲዮን ጨምሮ የቡና ማፍያና የመመገቢያ ቁሳቁስ ያለው ነው፡፡

* * *

የኔና ያንተ ቤት…

በኔና ባንተ ቤት ዘመን በጠገበው

አንተ ባንደኛው ጥግ እኔ በሌላኛው ደግፈን በያዝነው

ብዙ ሚስጥር አለ ብዙ የእንባ ሰበብ

ብዙ ሐሴት አለ ብዙ ብዙ ረሃብ

በኔና ባንተ ቤት

ጉጉት በሞላበት

ጥረት በሞላበት

ብዙም ዝምታ አለ ለሰው የማንነገረው

ብዙም ጩኸት አለ ሀገር የሚሰማው

የሚደነቅበት ‹አጀብ› የሚያሰኘው፡፡

በኔና ባንተ ቤት

ጭንቀቴ ልብህን በከታተፈበት

ሕመምህ መንፈሴን ባወላገደበት

ብዙ መርዶ አልፈናል

ብዙ ሰው ገለናል…

ብዙ ጥፋት አለ ብዙ መተላለፍ

ብዙ ቁልምጫ ብዙ መዘላለፍ…

የኔና ባንተ ቤት… ዘመን የጠገበው

ይህን ሁሉ ችሎ ላመታት የቆመው

በ’ኛ ታምር ሳይሆን በፍቅር ብርታት ነው፡፡

ብሩክታዊት ጎሳዬ፤ ደመኛ ፍቅር 2007

* * *

የኾንሶ ባህላዊ ሕግ መገለጫዎች

የኾንሶ ባህላዊ ሕግ በተለያዩ መድረኮች ይገለጻል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ

ኡካንታ (የደቦ ሥራ)

ሰዎች ሥራ ሲሠሩ ጨዋታ ይፈልጋሉ፡፡ ከጨዋታዎች መካከል ባህላዊ ሕጐች ለምን ጉዳይ ምን እንደሚሉ ማወቅና በዚህም ችሎታ መወዳደርና መደናነቅ፣ እንዲሁም መተቻቸት አንዱ መንገድ ነው፡፡ በዚህም ሒደት ወጣቱ ትውልድ በተለይ ከትችቱ ለመዳን በማሰብ ስለባህል ሕጉ ለማወቅ ይጥራል፡፡

ሔሚታ (ሠርግ)

ሠርግ በራሱ የተለያዩ ሒደቶችና ሥርዓቶ አሉት፡፡ የሠርግ ሥነ ሥርዓቶች ራሳቸው የባህል ሕጉ አንዱ አካል ናቸው፡፡ በመሆኑም ከሠርግ ጋር ተያይዞ የሚኖሩት የባህል ሕጉ ጉዳዮች በሠርግ ጊዜ ሁሉም አውቆም ይሁን ሳያውቅ ይማራቸዋል፡፡ ያውቃቸዋል፡፡

ፓየታ (የለቅሶ ቤት)

ከለቅሶ ሥርዓት አንስቶ ሌሎች አያሌ ባህላዊ ሕጐች ይነሳሉ፣ ይወሳሉ፡፡ የሰው ልጅ በሆነ ባህላዊ መድረክ ሲሰባሰብ ስለባህሉ፣ ታሪኩ፣ ወጉ…ማውራቱ የተለመደ በመሆኑ ኾንሶዎችም በለቅሶ ቤት ስለ ባህላዊ ሕጋቸው አውቀውም ሆነ ሳያውቁት ብዙ ይማራሉ፡፡

ኾራ (በበጋ ወራት የሚከናወን ዓመታዊ ክብረ በዓል)

ይህ በዓል ሰፊ ሽፋን ያለውና ደማቅ በመሆኑ ብዙ የባህላዊ ሕግ እውቀቶች የሚገበዩበት ነው፡፡ ሥነ ሥርዓቱ ዓመታዊ የሕዝቡ ሕይወት፣ ስኬትና ድክመት የሚፈተሽበት፣ ለቀጣዩ ዓመት የተሻለ ዘመንነት የሚመኙበት ነው፡፡ ጭፈራውም ወጣቱን ሁሉ የሚመስጥ ስለሆነ በመድረኩ ላቅ ያሉ የባህል ሕጉ ትምህርቶች ይገበያሉ፡፡

መና ፖቃላ (የፖቃላ ሞትና የቀብር ሥነ ሥርዓት)

በኾንሶ ፖቃላ (የጐሳ መሪ) ሲሞት ሳይቀበር ለረጅም ጊዜ ይቆያል፡፡ አያሌ ሥነ ሥርዓቶችም ይካሄዱለታል፡፡ በእነዚህም መድረኮች ሕዝቦች ስለባህላቸው፣ የፖቃላ የአስተዳደርና የዳኝነት ሥርዓታቸው፣ ስለሚተካው መሪያቸው ብዙ እውቀትና ሐሳብ የሚለዋወጡበት መድረክና ጊዜ ነው፡፡

የሞራ ግንኙነት

ሞራ (የችሎት ቦታ) አገልግሎቱ ብዙ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ አንዱ የትምህርት መድረክነቱ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ በየፖሊታው (አንባ መንደሩ) ብዙ ሞራዎች የሚገኙ ሲሆን ነዋሪው በየቀኑ ይገኝባቸዋል፣ ውይይቶ፣ ምክክሮች፣ ስብሰባዎች ሲያስፈልጉ ይካሄድባቸዋል፡፡ እንደዚሁም በዕረፍት ጊዜ ሞራ ሄዶ መጫወት የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከሚነሱ ጉዳዮች ውስጥ አብዛኛው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከባህል ሕጉ ጋር የተገናኙ መሆናቸው የሚጠቀስ ነው፡፡

የጨቃ ቤት

ጨቃ የኾንሶ ባህላዊ መጠጥ ነው፡፡ በከተማ በገጠር በየቀኑ በስፋት የሚጠጣ ነው፡፡ በአንድ ፓሌታ ውስጥ ብዙ የጨቃ ቤቶች ሲኖሩ ሴት ወንድ ሳይል ተሰባስቦ ይጠጣባቸዋል፡፡ በጨቃ ቤት ዝምታ የለም፡፡ ማናቸውም ጉዳዮች ይነሳሉ፡፡ ይጣላሉ፡፡ ውይይቱ ወይም ክርክሩ የጋራ ነው፡፡ በየቀኑ በጨቃ ቤት የሚነሱ ጉዳዮች ሲታሰቡ የጨቃ ቤት የባህል ሕጉ ዋነኛ ትምህርት ቤት ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ክርባ (በዘፈኖች)፣ ሲግማይታ (በእረኛ እንጉርጉሮ)፣ ፖራ ቢሻ (ውኃ በሚቀዱ ሴቶች እንጉርጉሮ) ይገለጻል፡፡

አብዱልፈታህ አብደላህ፣ ሤራ አታ ኾንሶ (2006)

* * *

በኪሎ ሜትር የተለካው ፒዛ

ብዙዎች በጉጉት ይጠባበቁት የነበረው ፒዛ ከ18 ሰዓታት በኋላ በስሎ ወጥቷል፡፡ በፒዛ የምትታወቀው ጣሊያን 60 ምርጥ ፒዛ ሠሪዎቿን ያቀናጀችበት ይህ ፒዛ 1.59545 ኪሎ ሜትር (ወደ አንድ ማይል የሚጠጋ) ርዝመት አለው፡፡ ሚላን ውስጥ በተካሄደው ‹‹ሚላንስ ወርልድ ፌር 2015›› የተጋገረው ፒዛ በርዝመቱ ከዓለም አንደኛ ሆኖ በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ተመዝግቧል፡፡ 60ዎቹ ባለሙያዎች ያለ እንቅልፍ ለሰዓታት ያዘጋጁት ፒዛው ከ1.5 ቶን ሞዘሬላና 2ቶን የቲማቲም ድልህ የተሠራ ነው፡፡ ክብደቱም አምስት ቶን ይመዝናል፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ እንደገዘበው፣ ፒዛው ከዚህ ቀደም የዓለማችን ትልቁ ፒዛ የነበረውን የስፔን ባለ 1.1415 ኪሎ ሜትር ፒዛ በልጧል፡፡

* * *

አደንዛዥ ዕፅ በጡቷ ውስጥ አድርጋ ለማዘዋወር የሞከረች

አደንዛዥ ዕፆችን ከአንድ አገር ወደ ሌላ ለማዘዋወር የተለያዩ መንገዶች የሚጠቀሙ ግለሰቦች ጥቂት አይደሉም፡፡ ከሰሞኑ ከኮሎምቢያ፣ ቦጎታ የተሰማው ዜና አንዲት ሴት ጡቷ ውስጥ ኮኬይን አስቀብራ ስተዘዋወር መያዟን ይፋ አድርጓል፡፡ ፓውላ ዳይኒላ የ22 ዓመት ወጣት ናት፡፡ 1.5 ኪሎ ግራም የሚመዝን ፈሳሽ ኮኬይን ይዛ ወደ ስፔን ልትጓዝ ስትል ነው በቦጎታ አየር ማረፊያ የተያዘችው፡፡ ሮይተርስ የአየር ማረፊያውን ኰሎኔል ዲያጐ ሮስሮ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ፓውላ ከመያዟ አስቀድሞ ፊቷ ላይ ፍርኃት ይነበብ ነበር፡፡ መሸበሯ ያጠራጠራቸው የጥበቃ ሠራተኞችም ከሠልፈኞቹ ነጥለው ፈትሸዋታል፡፡

የፓውላ ኤክስሬ በቅርቡ የጡት ቀዶ ጥገና እንዳደረገች ያመለክታል፡፡ እሷም ምንነቱ ያልታወቀ ዕፅ ወደ ባርሴሎና እንድትወስድ በጡቷ እንደተቀበረ ተናግራለች፡፡ ቀዶ ጥገናው የተደረገላት እዛው ኮሎምቢያ ፒሬራ በተባለ ከተማ በሚገኝ ክሊኒክ ሲሆን፣ የተያዘችበት ቦጐታ ከተማ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ዕፁ ከሰውነቷ ተወግዷል፡፡ በሆስፒታሉ ውስጥ የኢንፌክሽን ሕክምና እየተደረገላትም ነው፡፡ በኮሎምቢያ በዓመት እስከ 300 ቶን ኮኬን የሚመረት ሲሆን፣ በፅዕ ዝውውር ቀዳሚ ቦታ ከያዙ አገሮች አንዷም ናት፡፡   

* * *

ሚሊዮን ዶላር ያስገኘ የሎተሪ ስጦታ

በአሜሪካ ሐሪስበርግ ነዋሪ የሆነችው ክርስቲና ሞራህ የአባቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በ20 ዶላር ገዝታ ለአባቷ ያበረከተችው ሎተሪ፣ አንድ ሚሊዮን ዶላር ባለዕድል አድርጓቸዋል፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ እንደዘገበው፣ ሞራህ ለአባቶች ቀን ለአባቷ ምን መስጠት እንዳለባት ግራ ገብቷት ነበር፡፡ ጉዳዩን ለእናቷ ስታማክር፣ እናቷ ዴቢ ሞራህ ባለ 20 ዶላር የሎተሪ ትኬት እንድትገዛ ይነግሯታል፡፡

ሞራህ የገዛችውን ሎተሪ ከፖስት ካርድ ጋር አድርጋ ለአባቷ ታበረክታለች፡፡ የአባቶች ቀን በተከበረ በአምስተኛው ቀን የወጣው ሎተሪ፣ ለ61 ዓመቱ ዮሴፍ ሞራህ አንድ ሚሊዮን ዶላር አጐናጽፏል፡፡

ጡረታ ሊወጡ ግማሽ ዓመት ያህል የቀራቸው ጆሴፍ፣ ስለዕጣው ተጠይቀው ‹‹እስካሁን በእጄ አልገባም፣ ቼኩ በእጄ ሲገባ በሎተሪ አንድ ሚሊዮን ብር ማግኘቴን አምናለሁ፤›› ብለዋል፡፡  

R1582 Zinek Caption
Helen

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ