Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአሥራ አምስተኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምዝገባ ሰኔ 22 ይጀምራል

የአሥራ አምስተኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምዝገባ ሰኔ 22 ይጀምራል

ቀን:

 –  ከኃይሌ ተሳታፊዎች ጋር ይሮጣሉ

በመጪው ኅዳር 2008 ለሚከናወነው 15 ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከነገ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ምዝገባ እንደሚጀምር ዝግጅት ክፍሉ አስታወቀ፡፡

አሥር ኪሎ ሜትር በሚሽፍነፍነው የ2008 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የታላቁ ሩጫ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በውድድሩ የሚሳተፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ዝግጅት ክፍሉ ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በውድድሩ 40,000 ተመዝጋቢዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የውጪ አገር ተሳታፊዎችን በሚመለከት ይኼ መግለጫ እስከተጠሰበትና የምዝገባ ጊዜውም ይፋ ሳይደረግ 200 ተሳታፊዎች መመዝገባቸውም ተገልጿል፡፡ እስከ 700 የሚደርሱ የውጪ ተመዝጋቢዎች ይጠበቃሉም  ተብሏል፡፡

ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ምዝገባ የሚደረግባቸው ቦታዎች ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሥር ቅርንጫፎች ማለትም በንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ፣ በአፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ፣ በሜክሲኮ ቅርንጫፍ፣ በ22 ማዞሪያ ቅርንጫፍ፣ በቻይና አፍሪካ ቅርንጫፍ፣ በጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ፣ በአራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ፣ በስላሴ ቅርንጫፍ፣ በጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍና በመሐል ገበያ ቅርንጫፍ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ኅዳር 12 2008 ዓ.ም. በሚከናወነው 15ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከወትሮው ለየት ብሎ እንደሚቀርብ፣ ይኼውም ከሁለት አሥርት ዓመታት ባለፈ የውድድር ዘመኑ አራት የዓለም ሻምፒዮን፣ ሁለት የኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ እንዲሁም 27 የዓለም አዳዲስ ክብረወሰኞች በመሰባበር የሚታወቀውና የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ ኃይሌ ገብረሥላሴ ከ40,000 ተሳታፊዎች ጋር የሚሮጥ መሆኑ መነገሩ ነው፡፡ ኃይሌ በውድድሩ የሚሳተፈው ከሁለት ወር በፊት ኢንተርናሽናል ውድድሩን በማንችስተር ከተማ ካደረገ በኋላ ራሱን ከዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ በማግለሉና ይህንኑም በአገር ውስጥ ለ15ኛ ጊዜ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳትሮ በይፋ ለወገኖቹ ለማብሰር እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የምዝገባ ዋጋውን በተመለከተ ቫትን ጨምሮ 150,000 ብር ሲሆን፣ ይህም የውድድር እቃዎች ማለትም ቲሸርት፣ ሜዳሊያና ሌሎች ወጪዎች በመጨመራቸው መሆኑ ዝግጅት ክፍሉ አስታውቋል፡፡ ቀድመው ለሚመዘገቡ 1,000 የግል ተሳታፊዎች የመለማመጃ ቲሸርት በነፃ የሚሰጥ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በመጨረሻም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖንሰር አድራጊነት በሚከናወነው የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር የተባበሩት መንግሥታት በኢትዮጵያ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ዝግጅቱን በመጠቀም ለበጎ አድራጎት የሚሆን ገንዘብ የማሰባስብ ሥራ የሚሠራ ሲሆን፣ በድምሩ ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እንደሚሰጥ ጭምር ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...