Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

ከልጅነቴ ጀምሮ ለግንባታ በሚል ሰበብ ዙሪያውን ከታጠረው የድሮ ኳስ መጫወቻችን የአራዳ ሜዳ አጥር ሥር ተጠግቶ የሚለምን ‹‹ማየት የተሳነው›› የኔ ቢጤ ክፉኛ ልቤን ነካው።

የኔ ቢጤው እጅግ በሚያሳዝን ድምፁ መፅዋቾችን ይማፀናል። የሚያየውም ሆነ የሚሰማው ሰው አልነበረም። ምክንያቱም ግር ግር ከበዛበት መንገድ ወጣ ብሎ አጥሩን ተደግፎ፣ ፊቱንም በስህተት ወደ ግርግዳው አዙሮት ስለነበር ነው።

ያሉኝን ዝርዝር ሳንቲሞች ለቃቅሜ ስሰጠው ምርቃቱን አውርዶብኝ ልመናውን ቀጠለ። ትንሽ ቆሜ አየሁት። የሰጠሁትን ጥቂት ሳንቲሞች ለመፅዋቾች መጥሪያ እያንሿሿ ተጠቀመበት። ራቅ ካለው ግርግር መሀል በድምፁም ይሁን በሳንቲሞቹ መንሿሿት ለመመፅወት የመጣ የለም። እኔም ቢሆን በአጋጣሚ ከጀርባው የተለጠፈውን የፊልም ፖስተር ለማየት ነበር የተጠጋሁት።

- Advertisement -

ሥራ ፈትቼ ሳየው ቆየሁ። በመሀል ግርምት የጫረብኝን ነገር አስተዋልኩ። አንድ ዕድሜያቸው ወደ 70 የሚጠጋ አዛውንት መነኩሴ አጠገቡ ደርሰው፣ መቋሚያቸውን ተደግፈው አሳዛኙን የየኔ ቢጤ ዜማ ማድመጥ ጀመሩ።

መነኩሴውን ለማየት አቋቋሜን አስተካከልኩ። እኚህ አባ ዓለም በቃኝ የመቋሚያቸውን የጫፍ መደገፊያ ጉንጫቸው ሥር ደግፈው ለቅሷቸውን ተያያዙት። ስላላመንኩ ተጠግቼ በደንብ አየኋቸው። የየኔ ቢጤው ዜማ እኔንም ተፈታተነኝ።

‹‹እግዜሩ ደግ ነው ዓይኔን የሰወረ፣ ለጋሹን ሰው ባየው አልለምን ነበረ፤›› በአሳዛኙ ዜማው ደጋግሞ ያላትን ስንኝ በጣም አስተዋልኳት። የለጋሽን ግርግር የበዛበት ሕይወት። የሰውን ፊት ማየት ይሉት ነገር ከባድ ፈተና። እሱን አለማየት ለካ ዕድል ነው አልኩ።

መነኩሴው እንባቸው መንታ መንታ እየሆነ ይወርዳል።  ጥቂት ከቆዩ በኋላ እንባቸውን ጠራርገው ወደ ግርግር የበዛበት የሕዝብ መተላለፊያ ሄዱ። በዓይኔ ሸሁዋቸው።

 እኚህ አባት ግር ግሩ መሀል ቆመው እጃቸውን ለልመና ዘረጉ። ‹ለካስ እርሳቸውም የኔ ቢጤ ናቸው› ስል አሰብኩ። የሰው ፊት የማየት ልምድ ያላቸው ያልመሰሉኝ መነኩሴ ቀልቤን ሳቡኝ። እንደ ጀመርኩት የሳቸውን ልመናስ ለምን አልሰማም? ብዬ ተጠጋኋቸው።

መነኩሴው እጃቸውን ከማወዛወዝ በቀር ምንም ቃል አያወጡም። አንድ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ሳንቲሞች ሰጣቸው። አሁን ሳንቲሙ ድምፅ አለው። የተለያዩ መንገደኞች አምስትም አሥርም ድፍን ድፍን ብርም ሰጧቸው።

ግርግሩ መሀል ሆኞ አሻግሬ ‹‹ማየት የተሳነውን›› የኔ ቢጤ አስተዋልኩት። ማንም የሚያየውና የሚመፀውተውም የለም። መነኩሴው ግን ሽርፍራፊ ሳንቲሞች እየሰበሰቡ እጃቸው መሙላት ጀምሯል። እኚህ መንፈሳዊ አባት ውስጤን በታላቅ ሐዘን የሞሉትና የሰው ፊት የገረፋቸው ለካ የሰበሰቡትም ለዓይነ ሥውሩ የኔ ቢጤ ነበር።

እየተጎተቱ ሄደው የሰበሰቡትን ገንዘብ አንድም ሳያስቀሩ ሰጡት። ምርቃቱንም ሳያስጨርሱት ወደ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገቡ። የሰው ፊት እየገረፋቸው ሕፃናትን፣ አራጋውያንንና አቅመ ደካሞችን ከሰው ፊት መገረፍ በማዳን ላይ የሚገኙትን ጥቂት ሰዎች አስቤ አምርሬ አለቀስኩ።

‹‹እግዜሩ ደግ ነው ዓይኔን የሰወረ፣ ለጋሹን ሰው ባየው አልለምን ነበረ፤›

(ያሬድ ሹመቴ፣ በፌስቡክ ገጹ እንዳሰፈረው)

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...