Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍርፍሬ ከናፍር

ፍሬ ከናፍር

ቀን:

‹‹ተቀፍድዶ የተያዘውን የፍትሕ እጅ በምናሻሽለው ሕግ ነፃ እናወጣዋለን፡፡››

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ የአገሪቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ ፊታቸው ላይ ቁጣ እየተንበለበለ የእጆቻቸውን መዳፎች ጨብጠው ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንቱ፣ በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሒሻም ባራካት ላይ ግድያ የፈጸሙት ታጣቂዎች በጠንካራ ሕግ ይዳኛሉ ብለዋል፡፡ አሁን ባለው ሕግ ፍትሕ እጁን በሰንሰለት ታስሯል ያሉት አልሲሲ፣ መንግሥታቸው ሕጉን አሻሽሎ ፍትሕ በፍጥነት ያረጋግጣል ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ባራካት በተሽከርካሪ ላይ በተጠመደ ከባድ ቦምብ በደረሰባቸው ጉዳት ሆስፒታል ሕክምና ሲደረግላቸው ነው ያረፉት፡፡ እ.ኤ.አ. በ2013 የሙስሊም ብራዘርሁድ ተወካይ የነበሩት ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ ከሥልጣን ከተወገዱ ወዲህ፣ ባራካት በጂሃዲስቶች የተገደሉ የመጀመሪያው የግብፅ ከፍተኛ ባለሥልጣን ናቸው፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት ሟቹ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሒሻም ባራካት ናቸው፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...