አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 4 መካከለኛ ጭልፋ (600 ግራም) በመቀቀያ አፈር ተቀቅሎ በደቃቁ የተከተፈ የጐመን ቅጠል
- 1 ኪሎ ግራም በክቡ ተስተካክሎ የተላጠ ትናንሽ ድንች
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
- 3 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
- 3 ፍሬው ወጥቶ የተገረደፈ ቃርያ
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
አዘገጃጀት
- ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ በነጩ ማብሰል፤
- ሽንኩርቱ ሲበስል ድንቹን ጨምሮ ማብሰል፤
- ርጥብ ቅመም መጨመርና ትንሽ ውኃ አድርጐ ማብሰል፤
- ቅቤና ጥቁር ቅመም ጨምሮ ማንተክተክና የደቀቀውን ጐመን መጨመር፤
- ድንቹ እንዳይፈርስ በጥንቃቄ አማስሎ በደንብ ሲበስል መከለሻ፣ ጨውና ቃርያ ነስንሶ ካስተካከሉ በኋላ ማውጣት፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)